በቀራንዮ ያደረገልኝ
Beqeraneyo Yaderegelegn
ትራክ 12 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ስለት ነበረብኝ ለኢየሱስ ለጌታ
እንዲህ ካረገልኝ እስራቴን ከፈታ
እንደመልካም አባት አንጀቱ ራርቶ
አይዞህ ልጄ አለኝ ሳልጮህ ገና ሰምቶ (፪x)
ሃጥያት እየሰራሁ እንዲያ እያደከምኩት
የመስቀል ላይ ጣሩን እየዘነጋሁት
ምህረት ቸርነቱ ግን ይከታተሉኛል
አባብለው አምጥተው ቤቱ ያገቡኛል
ፊቱ ያቆሙኛል
አዝማች · Chorus
በቀራንዮ ያደረገልኝ
ከሁሉ በላይ ትዝ እያለኝ
ከቅዱሳን ጋር እሰግዳለሁ
በአዲስ ዝማሬ አዜማለሁ
ቁጥር 2 · Verse 2
ከአቻምና አምና ከአምና ዘንድሮ
የጌታ ውለታ አያልቅም ተቆጥሮ
የምህረቱ ብዛት የፍቅር ጥልቀቱ
ከልቤ ውስጥ ገባ የእግዚአብሔር ምህረቱ
የጌታ ምህረቱ
የፍቅር ዓይኖቹን በእኔ ላይ ያቀና
በምክር እግሮቹን ወደኔ ያቀና
እጆቹን ዘርግቶ ባርኮኛልና
ይኸው መስዋእቴ ከነፍሴ ምሥጋና
ከልቤ ምሥጋና
አዝማች · Chorus
በቀራንዮ ያደረገልኝ
ከሁሉ በላይ ትዝ እያለኝ
ከቅዱሳን ጋር እሰግዳለሁ
በአዲስ ዝማሬ አዜማለሁ
ቁጥር 3 · Verse 3
የሚያስጨንቀኝን ከሳሼን አዋርዶ
ሳልመርጠው የመረጠኝ ሳልወደው እጅግ ወዶ
ከአባቱ ጋር ስፍራን የሚያዘጋጅልኝ
ባለውለታዬ ኢየሱስ ይክበርልኝ
ጌታ ይክበርልኝ
ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ ጌታን አክብሩክኝ
እግዚአብሔር ፍቅር ነው በሉ ዘምሩልኝ
የጌታ ውለታ መግለጫ ያላችሁ
እስኪ እናምልከው ዕልል እያላችሁ
ክበር እያላችሁ
አዝማች · Chorus
በቀራንዮ ያደረገልኝ
ከሁሉ በላይ ትዝ እያለኝ
ከቅዱሳን ጋር እሰግዳለሁ
በአዲስ ዝማሬ አዜማለሁ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
እስኪ ቆም ብላችሁ አስቡ ለአንድ አፍታ
እናንተን ለማዳን ስለሞተው ጌታ
በቀራንዮ መስቀል ላይ የተንጠለጠለው
ከዘላለም ጥፋት አንተን ለማዳን ነው
አንቺን/እኛን ለማዳን ነው (፪x)
አዝማች · Chorus
በቀራንዮ ያደረገልኝ
ከሁሉ በላይ ትዝ እያለኝ
ከቅዱሳን ጋር እሰግዳለሁ
በአዲስ ዝማሬ አዜማለሁ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ