የዋይታና የመራራ ለቅሶ ድምጽ
Yewaytana Yemerara Leqso Demtse
ትራክ 9 · 5:31 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የምትወደው ልጅህን ወደ ተራራ ውሰደው
በእዚያም ለእኔ ክብር መስዋዕት አድርገህ ሰዋው
ጌታ እንዲህ ይለኛል ብዬ ከቶ አልጠበኩም
ቢሆንም ሳስተያየው ከእርሱ ፍቅር አይበልጥም
እኔም ሳላወላውል ወደዚያ ስፍራ ደረስኩኝ
ልጄን ለመሰዋት መሰዊያውን ሰራሁኝ
እንጨትም ረበረብኩኝ ልጄን ይስሐቅ አሰርኩኝ
በዚያም አጋደምኩኝ እጄንም ዘረጋሁኝ
ድምጹ ከሰማይ መጣ ሲል እጅህን አትዘርጋ
አብርሃም እንደምትወደኝ በእውነት ዛሬ አየሁኝ
የእውነት በረከትን እባርክሃለሁኝ
ልጅህን ላልከለከልከኝ በራሴ ምላለሁኝ
አዝማች · Chorus
የዋይታና የመራራ ለቅሶ ድምጼን
መጽናናት ሲያቅተኝ በፊትህ ያለቀስኩትን
እግዚአብሔር ከሰማይ ሆኖ ተመለከተኝ
ድምጹንም አሰማኝ እንዲህ አለኝ
ዓይንህን ከእንባ ከልክል ድምጽህንም ከለቅሶ
በጣም ቶሎ ታያለህ እንባህ ከዓይንህ ታብሶ
ኦሆሆ ኦሆሆ ኦሆሆ ምርኮህም ተመልሶ
ቁጥር 2 · Verse 2
ፈርዖን ሲያሳድደኝ ዳግም ባሪያው ሊያደርገኝ
በሰረገላው ብዛት በሰልፉ ሲነሳብኝ
ቀይ ባሕርም ከፊቴ ሞልቶ ተደቅኖብኝ
ማለፊያ መንገድ ጠፍቶኝ በፍርሃት ተሞላሁኝ
ጌታ ግን ቃሉን ሰጠኝ ብርሃኑን አበራልኝ
ባሕሩን እንድትከፍለው በትርህን አንሳ አለኝ
እኔም ለቃሉ ታዘዝኩ በጌታ ላይ ተደገፍኩ
ባሕሩም ተከፈለ ጠላቴም ሰጥሞ ቀረ
አዝማች · Chorus
የዋይታና የመራራ ለቅሶ ድምጼን
መጽናናት ሲያቅተኝ በፊትህ ያለቀስኩትን
እግዚአብሔር ከሰማይ ሆኖ ተመለከተኝ
ድምጹንም አሰማኝ እንዲህ አለኝ
ዓይንህን ከእንባ ከልክል ድምጽህንም ከለቅሶ
በጣም ቶሎ ታያለህ እንባህ ከዓይንህ ታብሶ
ኦሆሆ ኦሆሆ ኦሆሆ ምርኮህም ተመልሶ
ቁጥር 3 · Verse 3
ከብዙ የጠላት ሴራ እኔ ነኝ ያተረፍኩህ
እንድታገለግለኝ ልቤን በአንተ ያሳረፍኩኝ
ብሎ እንደታማኝ ባሪያ ጌታ ስለቆጠረኝ
ወደ ነነዌ እንድሂድ መለዕክትን ሰጥቶ ላከኝ
እኔ ግን በምትኩ ተርሴስ ልሄድ ፈለኩ
ብዙ ዋጋ ከፈልኩ በመርከብ ተሳፈርኩ
እንዳልሰማ እየሆንኩኝ በፊትህ ኮበለልኩኝ
ቃሉን በመተላለፍ እግዚአብሔርን በደልኩኝ
እርሱ ግን መቼ ተወኝ አምርሮ ተከተለኝ
ነፋሳትን አዘዘ ማዕበሉን አስነሳብኝ
እንዲያውም ይባስ ብሎ ከባሕር ውስጥ ተጣልኩኝ
ሶስት ቀንና ሌሊት በዓሣ ሆድ አደርኩ
በመከራዬ ሳለሁ ወደእግዚአብሔር ጮህኩኝ
ይልቁንም በንስሃ ከእርሱ ጋር ተስማማሁ
ጌታዬም ይቅር አለኝ ዳግም ተጠቀመብኝ
ነነዌንና ጌታን ለማስታረቅ በቃሁኝ
አዝማች · Chorus
የዋይታና የመራራ ለቅሶ ድምጼን
መጽናናት ሲያቅተኝ በፊትህ ያለቀስኩትን
እግዚአብሔር ከሰማይ ሆኖ ተመለከተኝ
ድምጹንም አሰማኝ እንዲህ አለኝ
ዓይንህን ከእንባ ከልክል ድምጽህንም ከለቅሶ
በጣም ቶሎ ታያለህ እንባህ ከዓይንህ ታብሶ
ኦሆሆ ኦሆሆ ኦሆሆ ምርኮህም ተመልሶ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ