Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እግዚአብሔር ብርሃኔና

Egziabhier Berhaniena

ትራክ 2 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ከባርነት ቀንበር ያወጣኸኝ

እስራቴን ፈተህ የለቀከኝ

ምሥጋናዬን እንካ የእኔ ጌታ

እንዳንተ አላየሁም የሚረታ

የሕይወት ምንጭ ነህ ለተጠማ

እንዲሁም ብርሃን በጨለማ (፪x)

እግዚአብሔር ብርሃኔና መድሃኔቴ ነው (፪x)

ቀንበር ያከበደው በጫንቃዬ

የነፍሴ ፈላጊ ባላንጣዬ

እግዚአብሔር ከእግሬ ስር አስገዛልኝ

እንድቀጠቅጠው እደረገኝ

እግዚአብሔር ብርሃኔ መድሃኔቴ

ሁሌ ከእኔ ጋር ነው በሕይወቴ (፪x)

እግዚአብሔር ብርሃኔና መድሃኔቴ ነው (፪x)

ማዳኑ በዛልኝ ቸርነቱ

ከእኔ አላራቀም ምህረቱን

ከመንፈሱ ዘየትን እየቀባኝ

በአደባባዩ አከበረኝ

እዚህ ደርሻለሁና በጌታ

አዜምለታለሁ ጠዋት ማታ (፪x)

እግዚአብሔር ብርሃኔና መድሃኔቴ ነው (፪x)

የነፍሴ ፈላጊ ጠላቶቼ

የበረቱ አስጨናቂዎቼ

በሞት ጥላ እንዳልፍ ፈረዱብኝ

ግን ጌታ ታድጐ ሕይወትን ሰጠኝ

ሰልፉ ቢነሳብኝ ልቤ አይፈራም

ጌታ ብርሃኔ ነው ለዘላለም (፪x)

እግዚአብሔር ብርሃኔና መድሃኔቴ ነው (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ