ስለዚህ ሁልጊዜ ዘምራለሁ
Selezih Hulgizie Zemeralehu
ትራክ 6 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ትላንትና ለሊቱን በሥጋዬ ጥሬያለሁ
አሁን ግን መረቦቼን በቃልህ እጥላለሁ
የበረከት አምላክ ሆይ ስታዘዘው ቃልህን
ተትረፈረፍኩኝ ዛሬ አይቻለሁ ሃይልህን (፫x)
አዝማች · Chorus
ስለዚህ ሁልጊዜ ዘምርልሃለሁ
በምሥጋናህም ላይ ሌላ ጨምራለሁ
በጥሩ የዜማ ቃል ፊትህ እጫወታለሁ
አምላኬ ጌታዬ አመሰግናለሁ
አምላኬ ጌታዬ ከፍ አደርግሃለሁ
ቁጥር 2 · Verse 2
በዚህ ተራራ ታላቅ የሰባ ግብዣ እድርገህ
በብዙ ታምራቶች በደመና ተገልጠህ
ሌላውን አስክረሳ አስክመርጥ በዚህ መኖር
በብዙ ባርከኸኛል እግዚአብሔር ሆይ ክበር (፫x)
አዝማች · Chorus
ስለዚህ ሁልጊዜ ዘምርልሃለሁ
በምሥጋናህም ላይ ሌላ ጨምራለሁ
በጥሩ የዜማ ቃል ፊትህ እጫወታለሁ
አምላኬ ጌታዬ አመሰግናለሁ
አምላኬ ጌታዬ ከፍ አደርግሃለሁ
ቁጥር 3 · Verse 3
በትሬን ብቻ ይዤ ተሻገርኩ ዪርዳኖስን
የሁለት ክፍል ሰራዊት አርገኸኛል ዛሬ ግን
በጠላት ፊት ለፊት በዘይት ቀብተህ እራሴን
ላመላለስከኝ ጌታ ምን እላለሁ ተመስገን (፫x)
አዝማች · Chorus
ስለዚህ ሁልጊዜ ዘምርልሃለሁ
በምሥጋናህም ላይ ሌላ ጨምራለሁ
በጥሩ የዜማ ቃል ፊትህ እጫወታለሁ
አምላኬ ጌታዬ አመሰግናለሁ
አምላኬ ጌታዬ ከፍ አደርግሃለሁ
ቁጥር 4 · Verse 4
በዚያ ምድረ በዳ ላይ ብቻዬን ሳለሁኝ
በድንገት ከአጠገቤ ምንጩ ፈለቀልኝ
አለቆች እየቆፈሩ በቀራንዮ መስቀል ላይ
የዘላለም ሕይወት ምንጭ ጌታ ኢየሱስ ኤልሻዳይ (፫x)
አዝማች · Chorus
ስለዚህ ሁልጊዜ ዘምርልሃለሁ
በምሥጋናህም ላይ ሌላ ጨምራለሁ
በጥሩ የዜማ ቃል ፊትህ እጫወታለሁ
አምላኬ ጌታዬ አመሰግናለሁ
አምላኬ ጌታዬ ከፍ አደርግሃለሁ
ቁጥር 5 · Verse 5
በኤማኦስ መንገድ ላይ ተስፋ ቆርጠን ሳለን
ኢየሱስ እራሱ ቀድሞ ይሄድ ነበር አብሮን
የልብን ሃዘን ነቅሎ ለሚሞላን በደስታ
ምሥጋና ያንስብናል ለአምላካችን ለጌታ (፫x)
አዝማች · Chorus
ስለዚህ ሁልጊዜ ዘምርልሃለሁ
በምሥጋናህም ላይ ሌላ ጨምራለሁ
በጥሩ የዜማ ቃል ፊትህ እጫወታለሁ
አምላኬ ጌታዬ አመሰግናለሁ
አምላኬ ጌታዬ ከፍ አደርግሃለሁ
ቁጥር 6 · Verse 6
መስሎኝ ነበረ ለእኔስ በጠላቴ የተረታሁ
አቀበት ቁልቁለቱን ከቶ የማልወጣው
ከፍጥረት የታወቀው በድንቅ በታምራቱ
በብዙ ጥንቃቄው ጠብቆኛል በቤቱ
አኑሮኛል በቤቱ አክርሞኛል በቤቱ
አዝማች · Chorus
ስለዚህ ሁልጊዜ ዘምርልሃለሁ
በምሥጋናህም ላይ ሌላ ጨምራለሁ
በጥሩ የዜማ ቃል ፊትህ እጫወታለሁ
አምላኬ ጌታዬ አመሰግናለሁ
አምላኬ ጌታዬ ከፍ አደርግሃለሁ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ