እግዚአብሔር የተዋጋለት
Egziabhier Yetewagalet
ትራክ 4 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ማነው እንደ እኔ እግዚአብሔር የተዋጋለት?
ከፊቱ ወጥቶ ጠላትን ሁሉ ድል የነሳለት
ዝም ያሰኘለት?
ቁጥር 1 · Verse 1
ተራራ ላይ ሆኖ ጠላቴ ሲፎክር
የማይወድቅ መስሎት ሕይወቴን ሲያሸብር
በሰማይ የሚኖር አምላክ የሆነው
ከከፍታ አውርዶ በእግሬ ሥር ጣለው
አዝማች · Chorus
ማነው እንደ እኔ እግዚአብሔር የተዋጋለት?
ከፊቱ ወጥቶ ጠላትን ሁሉ ድል የነሳለት
ዝም ያሰኘለት?
ቁጥር 2 · Verse 2
ዘወትር ዕንቅፋትን በፊቴ ላይ ሲያኖር
ከበነዋል በቃ ! እያለ ሲፎክር
መብረቁን ልኮ ጌታ አወካቸው
ዳግም ላይነሱ በጥልቅ ጣላቸው
አዝማች · Chorus
ማነው እንደ እኔ እግዚአብሔር የተዋጋለት?
ከፊቱ ወጥቶ ጠላትን ሁሉ ድል የነሳለት
ዝም ያሰኘለት?
ቁጥር 3 · Verse 3
ነበረብኝ ብዙ ሸክም የሆነብኝ
ልቤንም አቅልጦት በጣም ያስጨነቀኝ
ጌታ ደርሶልኝ እኔን አስጥሎኛል
በቅዱሱ ማደሪያው እንዳርፍ እረድቶኛል
አዝማች · Chorus
ማነው እንደ እኔ እግዚአብሔር የተዋጋለት?
ከፊቱ ወጥቶ ጠላትን ሁሉ ድል የነሳለት
ዝም ያሰኘለት?
ቁጥር 4 · Verse 4
እንደዚህ እረድቶኝ ከጠላት ድኛለሁ
በማያልቅ ፍቅሩ ጸንቼ ቆሜያለሁ
ከእንግዲህ በቃ ጌታ ይቀድመኛል
ስለሚዋጋልኝ ማክበር ይገባኛል
አዝማች · Chorus
ማነው እንደ እኔ እግዚአብሔር የተዋጋለት?
ከፊቱ ወጥቶ ጠላትን ሁሉ ድል የነሳለት
ዝም ያሰኘለት?
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ