ላመስግነው
Lamesgenew
ትራክ 11 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ላመስግነው (፬x)
ምሕረቱ ብዙ ነው ፤ ምሕረቱ
ይቅርታው ብዙ ነው ፤ ይቅርታው
ቁጥር 1 · Verse 1
ይቅር ስላለኝ ብዙ በደሌን
ቆሜ ለመሄድ በቃሁኝ እኔ
በቀን ውሎዬ ምሕረቱ በዝቶ
ስሙን እንዳስብ ሆነኝ መከታ
አዝማች · Chorus
ላመስግነው (፬x)
ምሕረቱ ብዙ ነው ፤ ምሕረቱ
ይቅርታው ብዙ ነው ፤ ይቅርታው
ቁጥር 2 · Verse 2
ተከብቤያለሁ በእርሱ ቸርነት
ጠላቴ እንዳያይ በመግባት መውጣት
እጁን በላዬ ያወዛውዛል
ዛሬም ለነገ ምሕረቱ በዝቷል
አዝማች · Chorus
ላመስግነው (፬x)
ምሕረቱ ብዙ ነው ፤ ምሕረቱ
ይቅርታው ብዙ ነው ፤ ይቅርታው
ቁጥር 3 · Verse 3
ልዘምርለት ስሙን ላክብረው
ወዶ ያዳነኝ ጌታ ኢየሱስ ነው
ምሕረቱ እኔን ከቦኛልና
ለሥሙ ክብር ይሁን ምሥጋና
አዝማች · Chorus
ላመስግነው (፬x)
ምሕረቱ ብዙ ነው ፤ ምሕረቱ
ይቅርታው ብዙ ነው ፤ ይቅርታው
ቁጥር 4 · Verse 4
ኢየሱስ ምሕረቱ ለዘለዓለም ናት
በእርሱ ሆነልኝ ወደ ዓብ መግባት
ከቶ አልታጣም ዘወትር ከፊቱ
ከቁጣው ይልቅ በዝቷል ምሕረቱ
አዝማች · Chorus
ላመስግነው (፬x)
ምሕረቱ ብዙ ነው ፤ ምሕረቱ
ይቅርታው ብዙ ነው ፤ ይቅርታው
ቁጥር 5 · Verse 5
በፍርሃት ውስጥ በጭንቅ ተይዤ
የልቤን አምላክ ፊቱን ፈልጌ
ዘወር ብሎ መጣ እኔን አሰበኝ
ሥሙ ይባረክ! ፈጥኖ የታደገኝ
አዝማች · Chorus
ላመስግነው (፬x)
ምሕረቱ ብዙ ነው ፤ ምሕረቱ
ይቅርታው ብዙ ነው ፤ ይቅርታው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ