ላደረገልኝ መልካም ምሕረት
Laderegelign Melkam Meheret
ትራክ 5 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ስላደረገልኝ መልካም ምሕረት
አልተፈረደብኝ አቤት ደግነት!
ተትቶልኝ ብዙ በደሌ ሳይከፈለኝ
በቤቱ አለሁ ፀጋው ምሕረቱ ስለደገፈኝ
ከሰማይ ላለው እጄን አንስቼ
ክብር እሰጣለሁ ዛሬም ፊቱን አይቼ
ቁጥር 1 · Verse 1
እስቲ ልቁጠረው እርሱ ያደረገውን
ታላቅ ምሕረቱን የማይረሳውን
አሸጋገረኝ ምሕረቱ አሸጋገረኝ
አሸጋገረኝ ደግነቱ አሸጋገረኝ
አዝማች · Chorus
ስላደረገልኝ መልካም ምሕረት
አልተፈረደብኝ አቤት ደግነት !
ተትቶልኝ ብዙ በደሌ ሳይከፈለኝ
በቤቱ አለሁ ፀጋው ምሕረቱ ስለደገፈኝ
ከሰማይ ላለው እጄን አንስቼ
ክብር እሰጣለሁ ዛሬም ፊቱን አይቼ
ቁጥር 2 · Verse 2
እንዲህ የማረከኝ የእርሱ ምሕረት
ሁሌ ያኖረኛል በቤቱ በዕውነት
አልዘነጋውም ቸርነቱን አልዘነጋውም
አልዘነጋውም በጐነቱን አልዘነጋውም
አዝማች · Chorus
ስላደረገልኝ መልካም ምሕረት
አልተፈረደብኝ አቤት ደግነት!
ተትቶልኝ ብዙ በደሌ ሳይከፈለኝ
በቤቱ አለሁ ፀጋው ምሕረቱ ስለደገፈኝ
ከሰማይ ላለው እጄን አንስቼ
ክብር እሰጣለሁ ዛሬም ፊቱን አይቼ
ቁጥር 3 · Verse 3
የማያልቅ ነው የእርሱ ምሕረት
ከዕለት ወደ ዕለት ዕረፍት የሚሰጥ
የማያልቅ ነው ምሕረቱ የማያልቅ ነው
የማያልቅ ነው ቸርነቱ የማያልቅ ነው
አዝማች · Chorus
ስላደረገልኝ መልካም ምሕረት
አልተፈረደብኝ አቤት ደግነት!
ተትቶልኝ ብዙ በደሌ ሳይከፈለኝ
በቤቱ አለሁ ፀጋው ምሕረቱ ስለደገፈኝ
ከሰማይ ላለው እጄን አንስቼ
ክብር እሰጣለሁ ዛሬም ፊቱን አይቼ
ቁጥር 4 · Verse 4
ጽድቅ የለኝ እኔ የምመካበት
በቤቱ መኖር የምችልበት
ምሕረቱ ነው ዛሬም ለእኔ ምሕረቱ ነው
በጐነቱ ነው ዛሬም ለእኔ በጐነቱ ነው
አዝማች · Chorus
ስላደረገልኝ መልካም ምሕረት
አልተፈረደብኝ አቤት ደግነት!
ተትቶልኝ ብዙ በደሌ ሳይከፈለኝ
በቤቱ አለሁ ፀጋው ምሕረቱ ስለደገፈኝ
ከሰማይ ላለው እጄን አንስቼ
ክብር እሰጣለሁ ዛሬም ፊቱን አይቼ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ