ከአንተ በቀር
Kante Beqer
ትራክ 2 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ከአንተ በቀር ኃያል ማንም የለም
እግዚአብሔር ብርቱ ለዘለዓለም
የሚቋቋምህ ኦሆ! ማንም የለም
ስመ ብርቱ ነህ ጌታ ለዘለዓለም
ቁጥር 1 · Verse 1
ይዘመርልህ ጌታ ጌታ ነህ
ማነው እንዳንተ የተከበረ?
በኃይሉ ሥልጣን ያልተደፈረ
ከጥንት የነበረው ዛሬም ደግሞ ያለው
እኛ የምናመልከው ሥሙ እግዚአብሔር ነው
አልተለወጠም ዛሬም ሕያው ነው
የእኛ ኢየሱስ ብርቱ አምላክ ነው
አዝማች · Chorus
ከአንተ በቀር ኃያል ማንም የለም
እግዚአብሔር ብርቱ ለዘለዓለም
የሚቋቋምህ ኦሆ! ማንም የለም
ስመ ብርቱ ነህ ጌታ ለዘለዓለም
ቁጥር 2 · Verse 2
ምሕረት ዕውነቱ የተገለጠ
የእግዚአብሔር ልጅ ያልተለወጠ
ዕውነቱ ከምድር እስከ ሰማይ ያለው
ሰላምን ለሕዝቡ ሁሌ የሚናገረው
ያየነው ዕውነት እርሱ ታላቅ ነው
ተወዳዳሪ ምን መሳይ አለው?
አዝማች · Chorus
ከአንተ በቀር ኃያል ማንም የለም
እግዚአብሔር ብርቱ ለዘለዓለም
የሚቋቋምህ ኦሆ! ማንም የለም
ስመ ብርቱ ነህ ጌታ ለዘለዓለም
ቁጥር 3 · Verse 3
ጌታ እንዳንተ ማን ብርቱ አለ?
ሳይሰጋ ከቶ በክብር ያለ
በተዘረጋ ክንዱ ሁሉን በሚችለው
ተአምራት በመሥራት ስሙን ያስከበረው
የአብርሃም አምላክ ዛሬም ሕያው ነው
ኃያል ሥም ያለው ጌታ ጌታ ነው
አዝማች · Chorus
ከአንተ በቀር ኃያል ማንም የለም
እግዚአብሔር ብርቱ ለዘለዓለም
የሚቋቋምህ ኦሆ! ማንም የለም
ስመ ብርቱ ነህ ጌታ ለዘለዓለም
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ