Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እንዳንተ ማን ነው

Endante Man New

ትራክ 6 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

፣ኧረ እንዳንተ ማነው ? (፬x)

በጨለማ ብርሃን ነህ

በሃዘንም ደስታ ነህ

ለታመመው መድሃኒት ነህ

ፍፁም ፈውስም በእጅህ አለ

ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ !

እስከዚህ ያደረስኸኝ

እኔ ማነኝ ? (፬x)

ቤቴስ ምንድነው ?

የማይገባኝን ክብር በአንተ አገኘሁ

ጌታ ተመስገን !

ሁሉ በአንተ ሆኗል

ከእኔ የሆነ የለም

አንተን የታመነ መች ወድቋል?

ዘለዓለም በጥላህ ይኖራል

በምትችለው በአንተ መመካት

ይሻላል ፣ ይጠቅማል መኩራራት !

ተነሣሁ ከአመድ ከትቢያ

ረዳኸኝ አንተ ብርቱ ጌታ !

የዜማ ጊዜ ደረሰልኝ !

ስምህን ለማክበር በቃሁኝ !

፣ኧረ እንዳንተ ማነው ? (፬x)

በጨለማ ብርሃን ነህ

በሃዘንም ደስታ ነህ

ለታመመው መድሃኒት ነህ

ፍፁም ፈውሥም በእጅህ አለ

ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ !

እስከዚህ ያደረስኸኝ

እኔ ማነኝ ? (፬x)

ቤቴስ ምንድነው ?

ቅጥርን ማዘለል ፣ ማበርታት ታውቃለህ

ለደካማው ኃይልን ፣ ብርታት ትሰጣለህ

ማለዳ ፣ ማለዳ ኃይልህን

በመከራ ጊዜ ፣ ማዳንህ

የማይዘነጋ ነው ፍቅርህ

የየቀኑ ታላቅ ምክርህ

፣ኧረ እንዳንተ ማነው ? (፬x)

በጨለማ ብርሃን ነህ

በሃዘንም ደስታ ነህ

ለታመመው መድሃኒት ነህ

ፍፁም ፈውሥም በእጅህ አለ

ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ !

እስከዚህ ያደረስኸኝ

እኔ ማነኝ ? (፬x)

ቤቴስ ምንድነው ?

ያደረግኸው ለእኔ እጅጉን ብዙ ነው

ጌታ ተመስገን !

የውለታህም ልክ ከምለው በላይ ነው

እጅህ የማይደክም ሁልጊዜ

ጽኑ መከታ ነህ ለነፍሴ

ማረፍ በአንተ ብቻ ነው

ዘወትር ስምህን ማክበር ነው

፣ኧረ እንዳንተ ማነው ? (፬x)

በጨለማ ብርሃን ነህ

በሃዘንም ደስታ ነህ

ለታመመው መድሃኒት ነህ

ፍፁም ፈውሥም በእጅህ አለ

ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ !

እስከዚህ ያደረስኸኝ

እኔ ማነኝ ? (፬x)

ቤቴስ ምንድነው ?

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ