በሥሙ ጉልበት እታመናለሁ
Besemu Gulbet Etamenalehu
ትራክ 9 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
የእባቡን እራስ እቀጠቅጣለሁ!
ገና ሥራውን አፈራርሳለሁ!
በሥሙ ጉልበት እመታዋለሁ!
ዕቅድ ሃሣቡን አፈራርሳለሁ!
በኢየሱስ ሥም እመታዋለሁ!
ዘወትር ምክሩን አበላሻለሁ!
ቁጥር 1 · Verse 1
ገና ገና ከጅምሩ እኔን የመረጠኝ
የወደደኝ ያከበረኝ ሙሉ መብት የሰጠኝ
የከሳሼን ግንባር መቶ ፊቴ የዘረረው
የማመልከው እግዚአብሔር ያለ የሚኖረው
አዝማች · Chorus
የእባቡን እራስ እቀጠቅጣለሁ!
ገና ሥራውን አፈራርሳለሁ!
በሥሙ ጉልበት እመታዋለሁ!
ዕቅድ ሃሣቡን አፈራርሳለሁ!
በኢየሱስ ሥም እመታዋለሁ!
ዘወትር ምክሩን አበላሻለሁ!
ቁጥር 2 · Verse 2
ለነአብርሃም ለነይስሐቅ አምላክ የሆናቸው
ሲድራቅ ሚሳቅ አብደናጐም ከእሣት ያወጣቸው
ለነጳውሎስ በደማስቆ ተገልጦ የታያቸው
እርሱ እኮ ነው የእኛ ጌታ ሥልጣን በእጁ ያለው
አዝማች · Chorus
የእባቡን እራስ እቀጠቅጣለሁ!
ገና ሥራውን አፈራርሳለሁ!
በሥሙ ጉልበት እመታዋለሁ!
ዕቅድ ሃሣቡን አፈራርሳለሁ!
በኢየሱስ ሥም እመታዋለሁ!
ዘወትር ምክሩን አበላሻለሁ!
ቁጥር 3 · Verse 3
ኤልያስን የሚሰማ ሲጣራ በቅጽበት
ድንቅ አድራጊ ኃያል ጌታ የሚመልስ በእሣት
አያሳፍር የበረታው በብርታቱ ታምኖ
ያኖረናል እየሠራ ጠላትን አባሮ
አዝማች · Chorus
የእባቡን እራስ እቀጠቅጣለሁ!
ገና ሥራውን አፈራርሳለሁ!
በሥሙ ጉልበት እመታዋለሁ!
ዕቅድ ሃሣቡን አፈራርሳለሁ!
በኢየሱስ ሥም እመታዋለሁ!
ዘወትር ምክሩን አበላሻለሁ!
ቁጥር 4 · Verse 4
እግዚአብሔር ዓብ ለአንድ ልጅ ሙሉ መብት የሰጠው
ጌታ ኢየሱስ ለእኛ ደግሞ እንዲሁ አሳለፈው
በደዌ አልጋ ለማቀቀው በእሥራት ለኖረው
መፍትሔ አለው የኢየሱስ ሥም ከእሥር ገላጋይ ነው
አዝማች · Chorus
የእባቡን እራስ እቀጠቅጣለሁ!
ገና ሥራውን አፈራርሳለሁ!
በሥሙ ጉልበት እመታዋለሁ!
ዕቅድ ሃሣቡን አፈራርሳለሁ!
በኢየሱስ ሥም እመታዋለሁ!
ዘወትር ምክሩን አበላሻለሁ!
ቁጥር 5 · Verse 5
የአምላኬ ሥም የጸና ነው ፣ ዛሬም ለዘለዓለም
የሚሠራ ኃይሉ ፣ ከቶ ጉልበቱ የማይደክም
በሰማይም በምድርም ያሻውን ያደርጋል
የሚከለክለው የለም ፣ በሥልጣን ይሠራል
አዝማች · Chorus
የእባቡን እራስ እቀጠቅጣለሁ!
ገና ሥራውን አፈራርሳለሁ!
በሥሙ ጉልበት እመታዋለሁ!
ዕቅድ ሃሣቡን አፈራርሳለሁ!
በኢየሱስ ሥም እመታዋለሁ!
ዘወትር ምክሩን አበላሻለሁ!
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ