ሲረዳኝ አይቼዋለሁ
Siredagn Ayechewalehu
ትራክ 8 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ሲረዳኝ አይቼዋለሁ ፣ ጌታን ኢየሱስን
ሲያግዘኝ አይቼዋለሁ ፣ ጌታን ኢየሱስን
ሲያቆመኝ አይቼዋለሁ ፣ ጌታን ኢየሱስን
ሲመራኝ አይቼዋለሁ ፣ ጌታን ኢየሱስን
እስከ ዛሬ የረዳኸኝ
በድካሜ ኃይል የሆንኸኝ
በዝቶ ፀጋህ እዚህ መድረሴ
ሁሉ በአንተ ፣ መች በራሴ? (፬x)
ቁጥር 1 · Verse 1
የአምላኬ ምሕረቱ በዝቶልኝ
በቤቱ ዕድሜን ጨምሮልኝ
ለትላንት ስሰጋ የነበርኩ
አለሁኝ በጥላው ስለሆንኩ
የረዳኝን አመሰግናለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
ሲረዳኝ አይቼዋለሁ ፣ ጌታን ኢየሱስን
ሲያግዘኝ አይቼዋለሁ ፣ ጌታን ኢየሱስን
ሲያቆመኝ አይቼዋለሁ ፣ ጌታን ኢየሱስን
ሲመራኝ አይቼዋለሁ ፣ ጌታን ኢየሱስን
እስከ ዛሬ የረዳኸኝ
በድካሜ ኃይል የሆንኸኝ
በዝቶ ፀጋህ እዚህ መድረሴ
ሁሉ በአንተ ፣ መች በራሴ? (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እጆቼን በክንዱ ደግፎ
ጉልበቴን በክብሩ አጽንቶ
መንፈሱን እጥፍ አድርጐልኛል
በክብሩ ክብሩን ገልጦልኛል
የረዳኝን አመሰግናለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
ሲረዳኝ አይቼዋለሁ ፣ ጌታን ኢየሱስን
ሲያግዘኝ አይቼዋለሁ ፣ ጌታን ኢየሱስን
ሲያቆመኝ አይቼዋለሁ ፣ ጌታን ኢየሱስን
ሲመራኝ አይቼዋለሁ ፣ ጌታን ኢየሱስን
እስከ ዛሬ የረዳኸኝ
በድካሜ ኃይል የሆንኸኝ
በዝቶ ፀጋህ እዚህ መድረሴ
ሁሉ በአንተ ፣ መች በራሴ? (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ሲማማል ጠላቴ ሊጥለኝ
ቀንቶብኝ ጌታ ስላለኝ
ቢወጣ ቢወርድ መች ይችላል?
ኢየሱስ ለእኔ አጥር ሆኖኛል
የረዳኝን አመሰግናለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
ሲረዳኝ አይቼዋለሁ ፣ ጌታን ኢየሱስን
ሲያግዘኝ አይቼዋለሁ ፣ ጌታን ኢየሱስን
ሲያቆመኝ አይቼዋለሁ ፣ ጌታን ኢየሱስን
ሲመራኝ አይቼዋለሁ ፣ ጌታን ኢየሱስን
እስከ ዛሬ የረዳኸኝ
በድካሜ ኃይል የሆንኸኝ
በዝቶ ፀጋህ እዚህ መድረሴ
ሁሉ በአንተ ፣ መች በራሴ? (፬x)
ቁጥር 4 · Verse 4
በሠልፉ እርሱ ተሰልፎ
ተዋጊው እግዚአብሔር አልፎ
የጠላት ከፍታው ተመቷል
ለሥሙ ምሥጋና ይገባል
የረዳኝን አመሰግናለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
ሲረዳኝ አይቼዋለሁ ፣ ጌታን ኢየሱስን
ሲያግዘኝ አይቼዋለሁ ፣ ጌታን ኢየሱስን
ሲያቆመኝ አይቼዋለሁ ፣ ጌታን ኢየሱስን
ሲመራኝ አይቼዋለሁ ፣ ጌታን ኢየሱስን
እስከ ዛሬ የረዳኸኝ
በድካሜ ኃይል የሆንኸኝ
በዝቶ ፀጋህ እዚህ መድረሴ
ሁሉ በአንተ ፣ መች በራሴ? (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ