Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እንዲህ ያረክልኝ

Endih Yarekelegn

2000 · ትራክ 10 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ግዑዝ እንኳን ያመልክሃል የማያውቅህ የአንተን ፍቅር

እንኳን ቀምሶ ያጣጣመህ እንደ እኔ አይነት ፍጡር (፫x)

የሚያውቅህ ነው የሚያውቀው

የአንተ ፍቅር የገባው

እህል ውሃ ማያሰኘው

ከአንተ በቀር ሌላ አያምረው (፪x)

ግዑዝ እንኳን ያመልክሃል የማያውቅህ የአንተን ፍቅር

እንኳን ቀምሶ ያጣጣመህ እንደ እኔ አይነት ፍጡር (፫x)

ያየሁትን አይቼ ነው

እንዲህ አፌን ሞልቼ ምዘምረው

ሊካድ የማይቻል እውነትህ

ማርኮ አስቀርቶኛል ያ ፍቅርህ (፪x)

ግዑዝ እንኳን ያመልክሃል የማያውቅህ የአንተን ፍቅር

እንኳን ቀምሶ ያጣጣመህ እንደ እኔ አይነት ፍጡር (፫x)

ዝም ማለት እንዴት ያስችለኛል

የእግዚአብሔር ፍቅር ግድ ይለኛል

ለቀየረው ለርሱ የኔን ሕይወት

ከዚህ በላይ ምነው በሆንኩለት (፪x)

ግዑዝ እንኳን ያመልክሃል የማያውቅህ የአንተን ፍቅር

እንኳን ቀምሶ ያጣጣመህ እንደ እኔ አይነት ፍጡር (፫x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ