ክቡርና ቅዱስ ነው
Kiburena Qidus New
2000 · ትራክ 7 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ፅድቅና መንግሥትህ እንደምን ያምራሉ
ከአንተ ወድያ ሕይወት ለምን ያሰኛሉ
የአባትነትህ ፍቅርህ በኢየሱስ ያየነው
ማርኮ አስቀርቶናል ኑሮዋችን የአንተ ነው (፪x)
አዝማች · Chorus
ክቡርና ቅዱስ ኃያል
ልዑል አባት እግዚአብሔር
ከአንተ በቀር ማንም የለም
አልነበረም ደግሞ አይኖርም (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሥራህን እያየን እናደንቅሀለን
ሁልጊዜ ፍቅርህን ጌታ እናስባለን
መንፈስና ሥጋ ነፍሳችን ተስማምተው
ያመሰግኑሃል ክበር ጌታ ብለው (፪x)
አዝማች · Chorus
ክቡርና ቅዱስ ኃያል
ልዑል አባት እግዚአብሔር
ከአንተ በቀር ማንም የለም
አልነበረም ደግሞ አይኖርም (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ውለታህ አለብን ከልብ የማይጠፋ
እኛን የረዳኸን ኢየሱስ ክብርህ ይስፋ
ከቶ ምን አለና ለእኛ ያላደረከው
መድኃኒታችን ሆይ ክብራችን ከአንተ ነው (፪x)
አዝማች · Chorus
ክቡርና ቅዱስ ኃያል
ልዑል አባት እግዚአብሔር
ከአንተ በቀር ማንም የለም
አልነበረም ደግሞ አይኖርም (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ከፀሐይ ሰባት እጅ ድምቀህ ትታያለህ
ሁለንተናህ ውብ ነው ምንም አልጐደለህ
ለግርማዊነትህ ክብር እንሰግዳለን
ልዑል ሆይ ለሥምህ እንዘምራለን (፪x)
አዝማች · Chorus
ክቡርና ቅዱስ ኃያል
ልዑል አባት እግዚአብሔር
ከአንተ በቀር ማንም የለም
አልነበረም ደግሞ አይኖርም (፬x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ከአንተ በቀር ማንም የለም
አልነበረም ደግሞ አይኖርም (፪x)
አዝማች · Chorus
ክቡርና ቅዱስ ኃያል
ልዑል አባት እግዚአብሔር
ከአንተ በቀር ማንም የለም
አልነበረም ደግሞ አይኖርም (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ