Lealem Tilahun/Hailenem Yemiyastateqegn/Hailenem Yemiyastateqegn
2000 · ትራክ 2 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ሁሉን አርገህልኛል የቀረብኝ የለም
ሌላ የምልህ ባይኖረኝ እወድሃለሁኝ
ሌላ የምልህ ባይኖረኝ እወድሃለሁኝ
ቁጥር 1 · Verse 1
የሰማይን ጸጋ የምድርን በረከት
በሌላ አይደለም ባንተ ነው ያገኘሁት
ጽድቅና ሰላምን የመንፈስን ደስታ
አጎኛጽፈኸኛል የሰራዊት ጌታ
አዝማች · Chorus
ሁሉን አርገህልኛል የቀረብኝ የለም
ሌላ የምልህ ባይኖረኝ እወድሃለሁኝ
ሌላ የምልህ ባይኖረኝ እወድሃለሁኝ
ቁጥር 2 · Verse 2
ምን ያጠያይቃል መልካምነትህ
ለኔስ ጌታ ኢየሱስ በረከቴ ነህ
መወደድ ሲያንስህ ነው መቼ ይበዛብሃል
እንኳን እኔነቴ ዘሬ ይገዛልሃል
እየዋለ እያደር ታምራትህ በዛ
የነገስታት ንጉስ የጌቶችም ጌታ /2/
ምን እንልሃለን ማዳንህን እያየን
ከምስጋና በላይ ምስጋና እንሰዋለን
ምን እንለሃለን ምህረትህን እያየን
ከክብርም በላይ ክብርን እንሰጣለን
መልካም ማድረግን ማይታክትህ
አቤት እግዚአብሔር ቸርነትህ
ትላንት ያረከው ሳይበቃህ
ዛሬም ደገምከኝ አብዝተህ /2/
በክብር ላይ ሌላ ክብር በክብር ላይ አሃሃ
ቆርጬያለሁ ለመጨመር ከዚያም በላይ
አንደበቴን በምስጋና እየከፈትኩ ኦሆ
ለድል ጌታ የደል ዜማ አመጣለሁ
ተራሮችንም ትክክል
አደረክና እግዚአብሄር አሃሃ
የናሱን ደጆች ሰባብረህ
እኔን ለክብርህ አበቃኸኝ
በክብር ላይ ሌላ ክብር በክብር ላይ አሃሃ
ቆርጬያለሁ ለመጨመር ከዚያም በላይ
አንደበቴን በምስጋና እየከፈትኩ ኦሆ
ለድል ጌታ የደል ዜማ አመጣለሁ
አምላኬ መታመኛዬ ነህ ጌታዬ
ንጉሴ መደገፊያዬ ነህ አንባዬ /2/
ቁጥር 3 · Verse 3
ሃይልንም የሚያስታጥቀኝ
ቁጥር 4 · Verse 4
ቅጥሩንም የሚያዘልለኝ
እግሮቼን የሚያበረታ
የሚያቆመኝ በከፍታ
ዛረ ታሪኬ ተለውጥዋል
ጠላት እያየ ይቃጠላል አሃሃ
ጌታ ሰጥቶኛል መሻቴን
ዘይት ቀብቶ እራሴን
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ