Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እየዋለ እያደር

Eyewale Eyader

2000 · ትራክ 1 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ሁሉን አድርገህልኛል የቀረብኝም የለም

ሌላ ምልህ ባይኖረኝ እወድሃለሁ እኔም

ሌላ ምልህ ባይኖረኝ እወድሃለሁ እኔም (፪x)

የሰማይን ፀጋ የምድርን በረከት

በሌላ እኮ አይደለም ባንተ ነው ያገኘሁት

ጽድቅና ሰላምን የመንፈስን ደስታ

አጎናጽፈኅኛል የሰራዊት ጌታ (፪x)

ሁሉን አድርገህልኛል የቀረብኝም የለም

ሌላ ምልህ ባይኖረኝ እወድሃለሁ እኔም

ሌላ ምልህ ባይኖረኝ እወድሃለሁ እኔም (፪x)

ምን ያጠያይቃል መልካምነትህ

ለኔስ ጌታ ኢየሱስ በረከቴ ነህ

መወደድ ስይንስህ ነው መች ይበዛብሃል

እንኳን እኔነቴ ዘሬ የገዛልሃል

እየዋለ እያደር ታምራትህ በዛ

የነገስታት ንጉስ የጌቶቹ ጌታ (፪x)

ምን እንልሃለን ማዳንህን እያየን

በምስጋና በላይ ምስጋናን እንሰዋለን

ምን እንልሃለን ምሕረትህን እያየን

በክብርም በላይ ክብርን እንሰጣለን

መልካምን ማድረግ ማይታክትህ

አቤት እግዚአብሔር ቸርነትህ አሃሃ

ትላንት ያረከው ሳይበቃህ

ዛሬም ደገምከኝ አብዝተህ (፪x)

በክብር ላይ ሌላ ክብር በክብር ላይ አሃ

ቆርጫለሁ ለመጨመር ከዚያም በላይ

አንደበቴን በምስጋና እየከፈትኩ ኦሆ

ለድል ጌታ የድል ዜማን አመጣለሁ

እየዋለ እያደር ታምራትህ በዛ

የነገስታት ንጉስ የጌቶቹ ጌታ (፪x)

ምን እንልሃለን ማዳንህን እያየን

በምስጋና በላይ ምስጋናን እንሰዋለን

ምን እንልሃለን ምሕረትህን እያየን

በክብርም በላይ ክብርን እንሰጣለን

ተራሮችንም ትክክል አደረክና እግዚአብሔር አሃ

የነሃሱን ደጆች ሰባብረህ እኔን ለክብር አበቃህ (፪x)

በክብር ላይ ሌላ ክብር በክብር ላይ አሃ

ቆርጫለሁ ለመጨመር ከዚያም በላይ

አንደበቴን በምስጋና እየከፈትኩ ኦሆ

ለድል ጌታ የድል ዜማን አመጣለሁ

አምላኬ መታመኛዬ ነው ጌታዬ

ንጉሴ መደገፊያዬ ነው አምባዬ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ