እወድሃለሁ
Ewedihalehu
2000 · ትራክ 3 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እወድሃለሁ አጅግ አብዝቼ
ከልቤ ጋራ እጄን አንስቼ
በምን ቋንቋ ነው ከቶ ምገልጸው
የልቤ አምላክ ሆይ ፍቅርህ ብርቱ ነው (፪x)
አዝማች · Chorus
ቃላት ባገኘሁና
ባወራው የአንተን ምስጋና
የልቤ በደረሰልኝ
አምላኬ አንተው ከብረህልኝ
ቁጥር 2 · Verse 2
የሚያስፈልገኝ አንድ ነገር
እርሱም አንተው ነህ ጌታ እግዚአብሔር
አንተን ካገኘሁ ጠግቤ አድራለሁ
ስለዚህ አምላኬ እወድሃለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
ቃላት ባገኘሁና
ባወራው የአንተን ምስጋና
የልቤ በደረሰልኝ
አምላኬ አንተው ከብረህልኝ
ቁጥር 3 · Verse 3
መላ እኔነቴ አንተን ይወዳል
በቀን በለሊት ልቤ ያስብሃል
ያላንተ መኖር አይሆንልኝም
ሕይወቴ አንተ ነህ ሌላም የለኝም (፪x)
አዝማች · Chorus
ቃላት ባገኘሁና
ባወራው የአንተን ምስጋና
የልቤ በደረሰልኝ
አምላኬ አንተው ከብረህልኝ
ቁጥር 4 · Verse 4
የእግዚአብሔር ልጅ መድህኔ
ሕይወቴ ነህ አንተ ለእኔ (፪x)
ሕይወት ተገለጠ እኔም አይቻለሁ
ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሼ አውቄያለሁ
እግዚአብሔር አምላክ ነው እኔም በርቶልኛል
ታዲያ ከእርሱ ፍቅር ማንስ ይለየኛል
አዝማች · Chorus
የእግዚአብሔር ልጅ መድህኔ
ሕይወቴ ነህ አንተ ለእኔ
ቁጥር 5 · Verse 5
የእግዚአብሔር ልጅ መድህኔ
ሰላሜ ነህ አንተ ለእኔ
ሰው አንተን ካገኘ ምን ያስፈልገዋል
እፎይ ብሎ አርፎ ተደላድሎ ይኖራል
ፍቅርህ የሚያጠገብ ልብን የሚያረካ
የመኖር ትርጉሙ ጌታ አንተ ነህ ለካ
አዝማች · Chorus
የእግዚአብሔር ልጅ መድህኔ
ሕይወቴ ነህ አንተ ለእኔ (፪x)
ቁጥር 6 · Verse 6
ዕረፍቴ ነህ አንተ ለእኔ
ሰላሜ ነህ አንተ ለእኔ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ