Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አንተ ትበልጥብኛለህ

Ante Tebeltibignaleh

2000 · ትራክ 5 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ለእኔስ ከአንተ ሚበልጥ ወዳጅ የለኝም

ፍቅርህ ዛሬም ትኩስ ነው

በልቤ ከቶ አይበርድም (፪x)

በመንፈስ ቅዱስ በልቤ የፈሰሰው

አቤቱ ፍቅርህ መተኪያ የለው (፪x)

ብዙ ውሆች እንኩዋን ሊያጠፉት አልቻሉም

ግሩም ነው ግሩም ነው ፍቅርህ አይነገርም

ለእኔስ ከአንተ ሚበልጥ ወዳጅ የለኝም

ፍቅርህ ዛሬም ትኩስ ነው

በልቤ ከቶ አይበርድም (፪x)

የብርሃን አባት የእኔ መመኪያ

ፍቅርህ ሁሌ አዲስ ነው ከልቤ ማይጠፋ (፪x)

አንተን አንተን እንጂ ማንንም አልልም

አምላኬ ጌታዬ እኔስ አልጠግብህም

ለእኔስ ከአንተ ሚበልጥ ወዳጅ የለኝም

ፍቅርህ ዛሬም ትኩስ ነው

በልቤ ከቶ አይበርድም (፪x)

የነፍሴ ጥጋብ የሕይወቴ አለኝታ

መጠጊያዬ ነህ ብሩኩ ጌታ (፪x)

ነፍሴን በምሕረትህ አድነሃልና

የመድህንቴ አምላክ ይድረስህ ምስጋና

ለእኔስ ከአንተ ሚበልጥ ወዳጅ የለኝም

ፍቅርህ ዛሬም ትኩስ ነው

በልቤ ከቶ አይበርድም (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ