ዙፋንህ የዘላለም ነው
Zufanih Yezelalem New
2000 · ትራክ 8 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አመታቶችህ ከቶ አያልቁም
የዘመንህ ቁጥር አይመረመርም
አልፋ ኦሜጋ ፊተኛ ኋለኛ
የእግዚአብሔር ልጅ ንጉስ ነህ ለእኛ
አዝማች · Chorus
ዙፋንህ የዘላለም ነው
መንግሥትህ ማንም አይሽረው
አንተ ግን አንተው ነህ ዘላለም
ኢየሱስ የሚመስልህ የለም (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ስልጣን የአንተ ነው መንግስት የአንተ ነው
አምላክና አባት አዳኝ የሆንከው
የሲኦልን ቁልፍ በእጅህ ይዘሃል
ጻድቅ ፈራጅ ነህ ክብር ይገባሃል
አዝማች · Chorus
ዙፋንህ የዘላለም ነው
መንግሥትህ ማንም አይሽረው
አንተ ግን አንተው ነህ ዘላለም
ኢየሱስ የሚመስልህ የለም (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ከጥንት ጀምሮ ምድርን መሰረትክ
በእጆች ሥራ ሰማይን ሰራህ
የፍጥረት ገዢ አምላክ አንተ ነህ
ሁሉም ያልፋሉ አንተ ግን ያው ነው
አዝማች · Chorus
ዙፋንህ የዘላለም ነው
መንግሥትህ ማንም አይሽረው
አንተ ግን አንተው ነህ ዘላለም
ኢየሱስ የሚመስልህ የለም (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ከስሞች በላይ ታላቅ ስም ይዘህ
በአባትህ ቀኝ በክብር ያለህ
የሁሉ ጌታ የሁሉ ንጉስ
የእኛም መድሃኒት አንተ ነህ ኢየሱስ
አዝማች · Chorus
ዙፋንህ የዘላለም ነው
መንግሥትህ ማንም አይሽረው
አንተ ግን አንተው ነህ ዘላለም
ኢየሱስ የሚመስልህ የለም (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ