እንግዳዬ
Engedaye
ትራክ 10 · 4:54 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እንዲ አልነበረም የቀድሞ ህይወቴ
በጭንቀት ሃዘን ጨልሞ ቤቴ
ሚረዳኝ የለም የሚያግዘኝ
ከጎኔ ሆኖ የሚያፅናናኝ
ድንገት ሳላስበው ቤቴ እንግዳ መጣ
የህይወቴን ታሪክ ሊቀይር ባንዳፍታ
ጋሻ ሆኜሃለው እስከዘላለም
አዝማች · Chorus
በፍፁም አትፍራ አለኝ እግዚአብሔር
እንድጋዬ ሆኖኝ አለኝታዬ
ህይወቴን ቀየረው እየሱስ ጌታዬ
ታሪክ ሆኖ ቀረ ድንገት ጨለማዬ/2
ቁጥር 2 · Verse 2
ሰመመን መሳዩን የቀድሞ ታሩኬን
ተሰማኝ ሲወጣ ከቤቴ
ያበቃውን ምዕራፍ የታጠረውን ልኬ
ቀጥሏል ሲመጣ አምላኬ
ተፈተው እሮጡ የታሰሩ እግሮቼ
እየሱስ ሲገባ ከቤቴ
ቀና ቀና አለ የዘመመው ቤቴ
ወዳጄ ሲገባ ከቤቴ
አዝማች · Chorus
እንድጋዬ ሆኖኝ አለኝታዬ
ህይወቴን ቀየረው እየሱስ ጌታዬ
ታሪክ ሆኖ ቀረ ድንገት ጨለማዬ/2
ቁጥር 3 · Verse 3
እየሱስ ቤታቸው ሲመጣላቸው
የተቀበሉት ሁሉ ከብረው ቀሩ/4
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ