ህይወት ደስ ይላል
Hiwet Des Yelale
ትራክ 7 · 5:14 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ህይወት ደስ ይላል ካንተ ጋራ
መኖር ደስ ይላል ካንተ ጋራ
በጣም ደስ ይላል ካንተ ጋራ
ሃይሌ ዝማሬዬ እግዚአብሔር እኮ ነው
እኔ አለመደሰት እንዴት እችላለው
ከሱ ጋራ ኖሮ ማንስ አዝኖ ያውቃል
ካሰበውም በላይ ደስታ በዝቶለታል
አዝማች · Chorus
በጌታ ደስ ደስ ይለኛል
በእየሱስ ደስ ደስ ይለኛል
ሁልግዜ ደስ ደስ ይለኛል
ባምላኬ ደስ ደስ ይለኛል
ቁጥር 2 · Verse 2
አሃ የህይወትን ትርጉም አሃ አጣጣምኩት ጌታ
አሃ ልቤንም ከፍቼ አሃ ያስገባሁህ ጌታ
አሃ መኖሬን ወደድኩት አሃ ካንተጋ ከርሜ
አሃ የዚ ሁሉ ምክኒያት አሃ አንተ ነህ አለሜ
አዝማች · Chorus
በጌታ ደስ ደስ ይለኛል
በእየሱስ ደስ ደስ ይለኛል
ሁልግዜ ደስ ደስ ይለኛል
ባምላኬ ደስ ደስ ይለኛል
ቁጥር 3 · Verse 3
ህይወት ደስ ይላል ካንተ ጋራ
መኖር ደስ ይላል ካንተ ጋራ
በጣም ደስ ይላል ካንተ ጋራ
አሃ ካንተ ጋራ መኖር አሃ በጣም ደስ ይለኛል
አሃ ልገልፀው የማልችል አሃ ሰላም ይሰማኛል
አሃ ሰው ሁሉ ጠየቀኝ አሃ ምን አገኘህ ብሎ
አሃ በጭንቀት ሰፈር ውስጥ አሃ ትስቃለህ ብሎ
ቁጥር 4 · Verse 4
ከእጅህ የበላሁት አይደለም ደስታዬ
ውስጤ የገባኸው አንተ ነህ እርካታዬ
በምድረበዳ ውስጥ ምንም በሌለበት
ደስ ደስ ይለኛል አንተን ሳስብበት
አዝማች · Chorus
በጌታ ደስ ደስ ይለኛል
በእየሱስ ደስ ደስ ይለኛል
ሁልግዜ ደስ ደስ ይለኛል
ባምላኬ ደስ ደስ ይለኛል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ