Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ቅዱስ

Kidus

ትራክ 9 · 4:25 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ካንተ በላይ ቅዱስ አልተገኝምና

ለስምህ የሚሆን ይድረስህ ምስጋና/2

ቅዱስ የተፈራህ ሃያል አምላክ ነህ

ምላስ ሁሉ ላንተ ይዘምርልህ

ጉልበት ሁሉ ላንተ ይንበርከክልህ

ማደሪያህም ቅዱስ ዙፋንህም ቅዱስ

መቅደስህም ቅዱስ አንተ እራስ ቅዱስ/2

እልፍ አላፍ መላዕክት ክብርህን እያዩ

ቅዱስ ቅዱስ ብለው ላንተ ይሰግዳሉ

ሰግደውልህ ላንተ ቀና ቀና ሲሉ

ቋንቋ መቀየሪያ ግዜም አላገኙ

ሃሌሉያ/8

ካንተ በላይ ቅዱስ አልተገኝምና

ለስምህ የሚሆን ይድረስህ ምስጋና/2

ቅዱስ የተፈራህ ሃያል አምላክ ነህ

ምላስ ሁሉ ላንተ ይዘምርልህ

ጉልበት ሁሉ ላንተ ይንበርከክልህ

ማደሪያህም ቅዱስ ዙፋንህም ቅዱስ

መቅደስህም ቅዱስ አንተ እራስ ቅዱስ/2

መቼም አይደክመኝም ላንተ ስሰግድልህ

እበረታለሁኝ ፊት ህንም ሳይ

በቅዱስ ስምህ እጓደዳለሁ

አምላኬ ነህና አመልክሃለሁ

ሃሌሉያ/16

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ