እርሴ አልቀይርም
Erese Alekeyrem
5:53 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ተገልጦልኛል ለእኔ አንድ እውነት
እየሱስ ብቻ ነው የዘላለም ህይወት
ተገልጦልኛል ለእኔ አንድ እውነት
እየሱስ ብቻ ነው የአለም መድሃኒት
ተገልጦልኛል አንድ እውነት
እየሱስ ብቻ ነው የዘላለም ህይወት
ተገልጦልኛል ለእኔ አንድ እውነት
እየሱስ ብቻ ነው የአለም መድሃኒት
ቁጥር 1 · Verse 1
እየሱስ ነው ዋና እየሱስ/4
የዚች ምድር ክብር ጥጉ ላይ ቢያደርሰኝ
ከሰው የተለየ እንጀራ አያበላኝ
አላማዬ አይደለም ከሰው በልጦ መኖር
እኔ ምናፍቀው የጌታን ክብር ነው
አላማዬ አይደለም ከሰው በልጦ መኖር
እኔ ምናፍቀው ያምላኬን ክብር ነው
አዝማች · Chorus
ወንጌል ስለ እርሱ ነው ስለእየሱስ/2
ወንጌል ስለልጁ ነው ስለእየሱስ/2
ቁጥር 2 · Verse 2
እርስ አልቀይርም እደጋግማለው እየሱስ እላለሁ/4
በዚ ምድር ስኖር እስትንፋሴ እስካለች
ኖሬ ጨርሳለሁ የገባኝን እውነት
እንኳን እኔ ሰዉ እግዚአብሔር ጨርሷል
እንድ ያለውን ልጁን ለአለም ሰቶታል/2
አዝማች · Chorus
እርስ አልቀይርም እደጋግማለው እየሱስ እላለሁ/6
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ