Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ተገርሜያለው

Tegeremelew

ትራክ 8 · 4:59 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በመወደዴ ተገርሜያለው/3

በመመረጤ ተደንቄያለው/3

የቁጣ ልጅ ነበርኩ የኖርኩ በጨላማ

በክፉ አለም ውስጥ ተግዤ ማነባ

እየሱስ ክርስቶስ ሆኖልኝ ቤዛ

ህይወትን አገኘው ሰላሜ ይኸው በዛ

አመሰግናለሁ ስለወደድከኝ

አመሰግናለሁ ስላከበርከኝ

አመሰግናለሁ ልጅህ ስላልከኝ

አመሰግናለሁ ስለመረጥከኝ

በመወደዴ ተገርሜያለው/3

በመመረጤ ተደንቄያለው/3

አለምን አትችፌ ነፍሴ እንድትጥፋ

ነበረ ምኞቱ ጠላቴ ሚለፋ

ጣልቃ ገባልኝ የይሁድ አንበሳ

ልጁ አደረገኝ ተከፍሎብኝ ዋጋ

አመሰግናለሁ ስለወደድከኝ

አመሰግናለሁ ስላከበርከኝ

አመሰግናለሁ ልጅህ ስላልከኝ

አመሰግናለሁ ስለመረጥከኝ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ