Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ማዳን የእግዚአብሔር

Madan Ye Egziabher

6:12 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እግዚአብሔር ብርቱ መታመኛዬ ነው መደገፊያዬ ነው

በእርሱ ዘላለም አርፋለው እፎይም እላለው/2

ማዳን የእግዚአብሔር ነው/2

ሃይል የእግዚአብሔር ነው/2

እነዚ በሰረገላቸው ይታመናሉ

እነዚያ በፈረሶቻቸው ይታመናሉ/2

እኛ ግን በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም

ከፍ ከፍ ከፍ ከፍ እንላለን/4

አሃ ከበባው ሲበዛ አሄ ጠላት ሲበረታ

አሃ እምነቴ ሲደክም አሄ መውጫውም ሲጠፋ

በጥቂቱም በብዙውም ማዳን የእግዚአብሔር ነው

አሃ በወጀቡ ላይ አሄ መንገድ ያለው ጌታ

አሃ ጩኸቴንም ሰምቶ አሄ ሊያድነኝም መጣ

በጥቂቱም በብዙውም ማዳን የእግዚአብሔር ነው

ማዳን የእግዚአብሔር ነው/2

ሃይል የእግዚአብሔር ነው/2

እነዚ በሰረገላቸው ይታመናሉ

እነዚያ በፈረሶቻቸው ይታመናሉ/2

እኛ ግን በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም

ከፍ ከፍ ከፍ ከፍ እንላለን/4

አሃ ማን አለ እንደኔ አሄ ምስጉን የሆነ ሰው

አሃ ከጠላቱ ዛቻ አሄ ባምላኩ የዳነ

በጥቂቱም በብዙውም ማዳን የእግዚአብሔር ነው

አሃ የዘላለም አምላክ አሄ ሆኖልኝ መከታ

አሃ ድሉ የኔ ሆነ አሄ የማታ የማታ

በጥቂቱም በብዙውም ማዳን የእግዚአብሔር ነው

ማዳን የእግዚአብሔር ነው/2

ሃይል የእግዚአብሔር ነው/2

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ