ያምራል
Yamerale
ትራክ 6 · 4:31 · አማርኛ
ተራራው ግዝፈቱን ሲነግረኝ
ሸለቆው ጥልቀቱን ሲያሳየኝ
ሰማይ ምድሩ ስፋቱን ሲያወራኝ
መደነቅን ሲጨምርብኝ
ይሄንን ሁሉ አይቼ ይሄንን ሁሉ ሰምቼ/2
ስረዳ እንደማልጨርሰው
ጀመርኩኝ ሰሪውን ላስበው/2
አዝማች · Chorus
የእርሱን ሃይልና ግርማ
ሞገሱን ውበቱን አየሁና
ከስራው ሰሪው እጅጉን ነው
ውበቱ እጅግ ያማረ ነው
ያምራል ያምራል የሱ ወበት ያምራል
ያምራል ያምራል የሱ ግርማ ያምራል/3
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ