እንጸልይ
Entseley
2011 · ትራክ 4 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ጊዜው እየከፋ ሲሄድ ሰው ምን ያደርጋል
ጥፋት ሲበዛ ወዴት ይሸሻል
መተማመን ጠፍቶ ጥላቻ ሲበረታ
የተለፋበት ሁሉ ድርምስምስ ሲል
ቀና ነው የተባለው ቅጡ ሲጠፋ
ሰው ግራ ተጋብቶ ጭንግር???ጭምር??? ሲለው
ወደማን ነው የሚያየው
አዝማች · Chorus
እንጸልይ ጸሎት የሚሰማ አምላክ አለ
እንጸልይ ሳንታክት
እንጸልይ ፍርድን የሚወድድ
አምላክ አለ በሰማይ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በድህነት ቀመር ተጠፍሮ
ህዝብ በድካም ጅራፍ ሲገረፍ
ሞትን እንደጨለማ ምድራችንን ሲከብ
አንዱ ከአንዱ ሲጋደል
አለቆች አልፈቱም ይህን እንቆቅልሽ
ከአዋቂቆችም ምክር አልተገኘም
ነገሥታት እነርሱ ተሰወረባቸው
ድንግዝግዝ አለ ቀኑ
አዝማች · Chorus
እንጸልይ ጸሎት የሚሰማ አምላክ አለ
እንጸልይ ሳንታክት
እንጸልይ ፍርድን የሚወድድ
አምላክ አለ በሰማይ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እንጸልይ
በስሜ የተጠሩ ህዝቤ
ራሳቸውን አዋርደው ቢጸልዩ
ከሰማይ ሆኜ እሰማለሁ
ምድራቸውን እፈውሳለሁ
ብሏል ጌታ (፪x)
አዝማች · Chorus
እንጸልይ ጸሎት የሚሰማ አምላክ አለ
እንጸልይ ሳንታክት
እንጸልይ ፍርድን የሚወድድ
አምላክ አለ በሰማይ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
እንጸልይ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ