ይሳካል
Yesakal
2011 · ትራክ 8 · አማርኛ
ህልመኛ ነኝ ህልም አለኝ የማያስቀምጠኝ
ባሳብኩት ቁጥር ውስጤን የሚያዘልለኝ
ለሌላው ባዋየው ቀድሞን ሁሌ ላይረዳኝ
ቀባጣሪ አስመሰለኝ ነገሬን ሲሰማኝ
ሁሁሁ አይ አይ (፪x)
እኖር ነበር በተከለለች ትንሽ ሜዳ
ትኩስ አየር ሲገባ ተሰማኝ በቅጥሩ ቀዳዳ
ተስፋ መልዕክት ይዞ ነው የመጣው ወደ እኔ
ሰብሬ የመውጣቴ ዛሬ ነው ቀኔ
ሁሁሁ አይ አይ (፪x)
(ማነው ያለው) አይሳካልሽም
(ማነው ያለው) መድረሻ የለሽም
(ማነው ያለው) ፍሬያማ አትሆኝም
(ማነው ያለው) ለሌላው አተርፊም
ይሳካል ይሆናል (፫x)
ለሚያምን ሁሉ ይቻላል (፫x)
ምንም የሚያቅተኝ የለም ለእኔ
ለሚያምን ሁሉ ይቻላል (፫x)
ምንም የሚያቅተኝ የለም ለእኔ
እንደ ንስር ክንፍ አውጥቼ???
እበራለሁ የኋላዬን ትቼ
እበራለሁ የኋላዬን ትቼ
ምንም የሚያቅተኝ የለም ለእኔ (፫x)
ምንም የሚያቅተኝ የለም ለእኔ
(ማነው ያለው) አይሳካልሽም
(ማነው ያለው) መድረሻ የለሽም
(ማነው ያለው) ፍሬያማ አትሆኝም
(ማነው ያለው) ለሌላው አተርፊም (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ