እርግጠኛ ነኝ
Ergetegna Negne
2011 · ትራክ 5 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ዝናቡ ከላይ ሲዘንብ
ጐርፉም ከታች ሲሞላ
ከመሃል ቆሜ እምተርፍ አልመስል
በንገዱን ባላውቀውም
እርሱ ብዙ መንገድ አለው
ይህ ይረዳኛል ያወጣኛል
አዝማች · Chorus
አንድ ነገር እርግጠኛ ነኝ
አንድ ነገር እርግጠኛ ነኝ
ብቻዬን አይደለሁም ኧረዳት አለኝ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሓሩሩ ቢያቃጥለኝ
ፊቴ ጠቁሮ ቢታይ
በረሃው ቅስሜን??? ቢያደክመኝም
ብቻዬን ብመስል እንኳን
ብቻዬን አይደለሁም
እወጣዋለሁ እረዳት አለኝ
አዝማች · Chorus
አንድ ነገር እርግጠኛ ነኝ
አንድ ነገር እርግጠኛ ነኝ
ብቻዬን አይደለሁም ኧረዳት አለኝ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ከጐኔ ነው ሁልጊዜ
ስለእኔ ግድ ይለዋል
ሃዘኔ ይሰማዋል የልቤን ያውቃል
የሚያስጨንቁኝ ሁሉ
በእርሱ ጉልበት ይፈታሉ
ሳልነግረው ይረዳኛል የልቤን ያውቃል
አዝማች · Chorus
አንድ ነገር እርግጠኛ ነኝ
አንድ ነገር እርግጠኛ ነኝ
ብቻዬን አይደለሁም ኧረዳት አለኝ (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ