Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

በሙሉ ልባችን እናመልክሃለን

Bemulu Lebachen Enamelkehalen

2011 · ትራክ 1 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እግዚአብሔር ምናመልክህ አስከብረኀን አይደለም

ብናመልክህ ብንሰግድልህ ስለተገባህ

የምትወደድ አምላክ ነህ ላወቀህ ለቀረበህ

ፍቅርህ ያዘምረናል ምሥጋናህ

እናመልክሃለን እግዚአብሔር

በሙሉ ሃይላችን በሙሉ ነፍሳችን

በሙሉ ልባችን እናመልክሃለን (፪x)

የዘለዓለማዊው መንግሥት አምባሳደሮች ልንሆን

ልትወደን ልትመርጠን አላፈርክብን

ልጆቼ ብለህ ጠራኀን አባ አባት ልንልህ ፈቀድክ

በድፍረት ፊትህን ልናይ ብቁ አደረግከን

እናመልክሃለን እግዚአብሔር

በሙሉ ሃይላችን በሙሉ ነፍሳችን

በሙሉ ልባችን እናመልክሃለን (፪x)

አባትነትህን ለማግኘት ከእኛ ምንም አላስከፈልክ

ይልቁን ልጅህን ሰጥተህ ከእኛ ታረቅህ

እንዴት ያለ ፍቅር ነው አንተ ለእኛ ያሳየኀው

ለአንተ መኖር መስገድ መቀኘት ሲያንስህ ነው

በሙሉ ሃይላችን በሙሉ ነፍሳችን

በሙሉ ልባችን እናመልክሃለን (፫x)

በሙሉ ልባችን እናመልክሃለን (፭x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ