ትልቅን ነገር አስባለሁ
Teleqen Neger Asebalehu
2011 · ትራክ 6 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በማዘን መተከዝ እግዚአብሔር ይከብር ይመስል
ምንድን ነው መርበትበት ሁልጊዜ መቆዘም
ጠላት ነው እንጂ በዚያ ደስ ደስ የሚለው
ምን ይጨምራል የአምላክን ሃይል መጠርጠር ነው
አዝማች · Chorus
አላንጐራጉርም አንገቴንም አልደፋም
እግዚአብሔር እንቅቶኛል ጊዜዬን አላጠፋም (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ምን አሸማቀቀኝ ምን አንገቴን አስደፋኝ
ጌታዬ ከእኔ ጋር ሆኖ እያየሁኝ
የማልፍበት ሁሉ እንደምናምን ቢመስልም
ነጥሬ እወጣለሁ ወደኋላዬ አልልም
አዝማች · Chorus
አላንጐራጉርም አንገቴንም አልደፋም
እግዚአብሔር እንቅቶኛል ጊዜዬን አላጠፋም (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የትም ስፍራ ብሆን የሚይዘኝ ምንም የለም
እሰራለሁ ስራ አለኝ ገና ያልጀመርኩት
ሲያየኝ ጠላቴ ለዐይኑ ባልሞላለትም
እግሬ የረገጠበት ሰላም አልሰጠውም
አዝማች · Chorus
አላንጐራጉርም አንገቴንም አልደፋም
እግዚአብሔር እንቅቶኛል ጊዜዬን አላጠፋም (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
የደከምኩ ስመስለው አሳድደዋለሁ
ተኛታለች ብሎ ሲል ህልምን አልማለሁ
ዛሬ አዘነች ሲል እዘምራለሁ
ከአምላኬ ተጣብቄ ግራ አጋባዋለሁ
አዝማች · Chorus
አላንጐራጉርም አንገቴንም አልደፋም
እግዚአብሔር እንቅቶኛል ጊዜዬን አላጠፋም (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ትልቅን ትልቅን ነገርን ሁልጊዜ
አስባለሁ አምላኬ ያንኑ ሲያደርግ አየዋለሁ
ከፍ ያለውን ከፍ ያለውን ነገርን ሁልጊዜ
አስባለሁ አምላኬ ያንኑ ሲያደርግ አየዋለሁ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ