እውነተኛ ወዳጅ
Ewnetegna Wedaj
2010 · ትራክ 4 · 4:49 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ከመፈጠሬ ከመታሰቤ ጀምሮ
የማትለወጥ የማትቀየር
ወረት የሌለበት አንተን ነው ያየሁት (፪x)
አዝማች · Chorus
እውነተኛ ወዳጅ ነህ
እውነተኛ አፍቃሪ (፪x)
የእኔስ ወዳጅ አንተ ነህ
ጊዜ/ዘመን የማይለውጥህ (፪x)
ለካስ ሁሉም ነገር ያልፋል
ለካስ አለው መጨረሻ
ለካስ እኔስ ወዳጅ አለኝ
በቃ ክፉ ቀን ማሸሻ
ቁጥር 2 · Verse 2
የሰው ልጅ ሆኖ የሰው
እየተባለ ማነው
ከሰማይ መጣ ከላይ
አላስችል ብሎት ሲያይ
ከሞት አወጣኝ ከሞት
ደርሶልኝ ካለሁበት
ተናገር ምንድን ነው ሲሉኝ
ለዚህ ነው ቃላት ያጠረኝ
ሰማይ ይናገር ምድርም
ስላንተ ላውራ ዘለዓለም (፪x)
አዝማች · Chorus
እውነተኛ ወዳጅ ነህ
እውነተኛ አፍቃሪ (፪x)
የእኔስ ወዳጅ አንተ ነህ
ጊዜ/ዘመን የማይለውጥህ (፪x)
ለካስ ሁሉም ነገር ያልፋል
ለካስ አለው መጨረሻ
ለካስ እኔስ ወዳጅ አለኝ
በቃ ክፉ ቀን ማሸሻ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ