ጌታ አለኝ
Gieta Alegn
2010 · ትራክ 2 · 5:55 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አምላኬ ነው የደገፈኝ እንዳልወድቅ በድካሜ
በሃሩሩ ጥላ ሆኖ ሳይለየኝ ከአጠገቤ
ከኋላዬ ሲከተለኝ እንቅፋቱ እንዳይጐዳኝ
የጠላዬን ወጥመድ ሰብሮ መኖሪያዬ ሆነልኝ
አዝማች · Chorus
አሃ ሲከተለኝ
አሃ ከኋላዬ
አሃ ሆኖልኝ ነው
አሃ ከለላዬ
አሃ ቀኑ ሲከፋ
አሃ ሲጨልም
አሃ ወንድም አለኝ
አሃ አይዞህ የሚል
ጌታ አለኝ (፲፪x)
ቅጥር ሆኖልኝ ነው እኔስ ያለፍኩት
አላልፈው ነበር ባይኖረኝ አባት
የትላንቱ ያን ጨለማ
ይገርመኛል ኧረ እንዴት (፪x) እንዴት ጠፋ
ሰባት እጥፍ የነደደው
እሳት ጠፍቷል ጌታዬን (፪x) ላመስግነው
ዋስትናዬ ሆኗል ለእኔ ጌታ (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ከለላዬ ሆኗል ለእኔ ጌታ (፬x)
የትላንቱን ያንን ወጀብ ቆም ብዬ ሳስበው
የዛሬን ቀን ስላየልኝ ፀጥ ያረገው ጌታ ነው
ለነገማ ዋስትና አለኝ ንፋስ ቢነፍስብኝ እላዬ
ከእንግዲህማ ልቤ አይፈራም ጌታ እኮ በታንኳዬ
አዝማች · Chorus
አሃ ሲከተለኝ
አሃ ከኋላዬ
አሃ ሆኖልኝ ነው
አሃ ከለላዬ
አሃ ቀኑ ሲከፋ
አሃ ሲጨልም
አሃ ወንድም አለኝ
አሃ አይዞህ የሚል
ጌታ አለኝ (፲፪x)
ቅጥር ሆኖልኝ ነው እኔስ ያለፍኩት
አላልፈው ነበር ባይኖረኝ አባት
የትላንቱ ያን ጨለማ
ይገርመኛል ኧረ እንዴት (፪x) እንዴት ጠፋ
ሰባት እጥፍ የነደደው
እሳት ጠፍቷል ጌታዬን (፪x) ላመስግነው
ዋስትናዬ ሆኗል ለእኔ ጌታ (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ቤተኛዬ ሆኗል የእኔ ጌታ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ