Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አመልክሃለሁ

Amelkehalehu

2010 · ትራክ 11 · 5:33 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ሞልቶ ለማይሞላ ለዚህ ዓለም ጉዳይ (፪x)

ጊዜ አላጠፋም ጐዶሎዬን ሳይ (፪x)

የበረከት ምንጩ መንገዱ ገብቶኛል (፪x)

ሁኔታው እያለ አምልከኝ ብሎኛል (፪x)

ልቤም እንዲህ ይለኛል

ኧረ ተነስ ይለኛል

አምልክ አምልክ ይለኛል

አመልክሃለሁ ጌታዬ አመልክሃለሁ

አመልክሃለሁ ኢየሱስ አመልክሃለሁ (፪x)

ተይ አልኳት ነፍሴን ተይ እንጂ (፪x)

ኢየሱስ ቆሞ ከደጅ

መዘመር ማምለክ ነው እንጂ (፪x)

አንተ የእግዚአብሔር ልጅ

ዛሬም መጣሁ ወደ ደጅህ

ምህረትህ በዝቶልኝ በሕይወቴ

ያቆመኝ ፀጋህ ነው መድኃኒቴ

አሁን አሁንማ እየዋለ ሲያድር (፪x)

ይገርመኝ ጀመረ የመስቀሉ ፍቅር (፪x)

ልቤን ያደረገው የዝማሬ ጓዳ (፪x)

ለካስ ተምሬ ነው የለብኝም ዕዳ (፪x)

ልቤም እንዲህ ይለኛል

ኧረ ተነስ ይለኛል

አምልክ አምልክ ይለኛል

አመልክሃለሁ ጌታዬ አመልክሃለሁ

አመልክሃለሁ ኢየሱስ አመልክሃለሁ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ