Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ፍቅር አሳየኸኝ

Feqer Asayehegn

2010 · ትራክ 13 · 4:40 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ባላጣኸው ቦታ ባላጣኸው ልብ

ኧረ እንዴት ወደድከኝ ገረመኝ ሳስብህ (፪x)

ማነው የወደደኝ ጠጋ ያረገኝ

ከመሞት አውጥቶ ፍቅር ያሳየኝ

ጌታ ነው (፫x) ጌታ

ጌታ ነው (፫x) ጌታ

የእኔማ ነገር የእኔስ ጉዳይ

ተፈጸመልኝ ጐልጐታ ላይ (፬x)

ምን ልበል ምን ላድርግ

ወዶኛል ያለ ልክ (፪x)

አንዴ ብቻ አይደለም

ብዙ ጊዜ ነው ጉልበት የሆንከኝ

እምነቴ ሲላላ ከጐኔ ቆመህ ያበረታኸኝ (፪x)

ወደድከኝ (፫x)

ይቅር አልከኝ(፫x)

መቼም መቼም መቼም ቢሆን

አልረሳውም የአንተን ፍቅርህን

ሰው ያረከኝ ያወጣኸኝ

ከጨለማው ከሞት ገደል (፪x)

ማነው የወደደኝ ጠጋ ያደረገኝ

ከመሞት አውጥቶ ፍቅር ያሳየኝ

ጌታ ነው (፫x) ጌታ

ጌታ ነው (፫x) ጌታ

ጌታ ነው (፫x) ጌታ

ጌታ ነው (፫x) ጌታ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ