ይደክመኛል መኖር
Yedekmegnal Menor
2010 · ትራክ 6 · 4:49 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
የሕይወቴ እረኛ ጌታ አለልኝ የማይተኛ (፪x)
የሕይወቴ ጠበቃ ጌታ እኮ ነው እንዳልሰጋ (፪x)
እኔማ ዕድለኛ ነኝ
አልፈራም ጌታ ስላለኝ
ዓለቱ ነው መሠረቴ
አይወድቅም በንፋስ ቤቴ
ከኢየሱስ ጋር ተዋድጄ
ይፈልቃል ሰላም ከደጄ
ለካ ለካ ጌታ እኮ ነው (፪x)
የትላንቱን ያንን ወጀብ ፀጥ ያረገው (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ኧረ እኔ
አመል ሆኖብኛል አመል (፪x)
ስነሳ ስቀመጥ ለክብርህ መዘመር
እንደዚህ ካልሆነ ይደክመኛል መኖር
ቁጥር 2 · Verse 2
የእኔ ነህ (፪x)
የእኔ ነህ ብልህ
ከመሞት/ከጭንቀት ያዳንከኝ
ጌታዬ እኮ ነህ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ከእንግዲህማ ወዳጅ አግኝቻለሁ
ከእንግዲህማ አብሮ የሚዘልቅ
ከእንግዲህማ እንዲህ ከወደደ
ከእንግዲህማ ጥሎ የማይሄድ (፪x)
አዝማች · Chorus
የሕይወቴ እረኛ ጌታ አለልኝ የማይተኛ (፪x)
የሕይወቴ ጠበቃ ጌታ እኮ ነው እንዳልሰጋ (፪x)
እኔማ ዕድለኛ ነኝ
አልፈራም ጌታ ስላለኝ
ዓለቱ ነው መሠረቴ
አይወድቅም በንፋስ ቤቴ
ከኢየሱስ ጋር ተዋድጄ
ይፈልቃል ሰላም ከደጄ
ለካ ለካ ጌታ እኮ ነው (፪x)
የትላንቱን ያንን ወጀብ ፀጥ ያረገው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ