Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ይቅርታ

Yeqerta

2010 · ትራክ 1 · 5:45 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አትተወኝ እባክህ አትራቀኝ

መንፈስህን ከውስጤ አትውሰደው (፪x)

ደግሞ እንደሚያውቅ

እንደሚያውቅ ልብ እንዳለው

ብዙ ደከምኩኝ እራሴን ታዝቤያለሁ (፪x)

ይቅርታ ይቅርታ

የእኔ አባት ይቅርታ

ይቅር በለኝና አስገባኝ

ዳግም ወደ ጉያህ (፪x)

ያኔ ያኔ አንተን ያወኩበት የልጅነት ኩራት

አይደክመኝም ፊትህን ስፈልግ ጠዋት ሆነ ማታ

ምነው አሁን ልቤን ምን አገኘው ምን ገባብኝ

ቆም ብዬ ራሴን ልጠይቀው ምህረት አርግልኝ

ወደ አይምሮዬ ልመለስና

ማረኝ ልበለው በርከክ ልበልና (፪x)

ይቅርታ ይቅርታ

የእኔ አባት ይቅርታ

ይቅር በለኝና አስገባኝ

ዳግም ወደ ጉያህ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ