ዓለም በቃኝ
Alem Beqagn
2010 · ትራክ 3 · 5:13 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
በዚህ ዓለም በዚህ ምድር ላይ
አዲስ ነገር አዲስ ነገር የለም ከኢየሱሴ በላይ
በዚህ ዓለም በዚህ ምድር ላይ
ሌላው ነገር አያስደንቀኝም ከኢየሱስ በላይ
በቃ ጌታ አለኝ
በቃ ተቀበለኝ በቃኝ
በቃ ጌታ አለኝ
በቃ ዓለም በቃኝ (፪x)
በቃኝ ነው ባሕር በአብ ቀኝ
ሊቀ ካህን በሰማይ አለልኝ
በቃኝ ነው ባሕር በአብ ቀኝ
የመረጠኝ በሰማይ አለልኝ
ቁጥር 1 · Verse 1
አልተሳሳትኩም (፪x) በምርጫዬ
ቀን ቆጠረና ዋጋ ከፈለኝ በተራዬ (፪x)
ፍፁም ነው (፪x) ለእኔ የታየልኝ በጐ ስጦታው
ልቤን ደስ የሚያሰኝ ከአብ ያገኘሁ ኢየሱሴ ነው
መጽሐፉ ነግሮኛል በሰማዩ ስፍራ ተቀምጠሃል ብሎ
ከዚህ የበለጠ ከዚህ የተሻለ ምን አለ ዘንድሮ
በዚህ ዓለም ካለው (፪x) ትልቅ ነኝ ካለው
በእኔ በትንሹ ከሁሉ ይበልጣል የተገለጠው (፪x)
አዝማች · Chorus
በዚህ ዓለም በዚህ ምድር ላይ
አዲስ ነገር አዲስ ነገር የለም ከኢየሱሴ በላይ
በዚህ ዓለም በዚህ ምድር ላይ
ሌላው ነገር አያስደንቀኝም ከኢየሱስ በላይ
በቃ ጌታ አለኝ
በቃ ተቀበለኝ በቃኝ
በቃ ጌታ አለኝ
በቃ ዓለም በቃኝ (፪x)
በቃኝ ነው ባሕር በአብ ቀኝ
ሊቀ ካህን በሰማይ አለልኝ
በቃኝ ነው ባሕር በአብ ቀኝ
የመረጠኝ በሰማይ አለልኝ
ቁጥር 2 · Verse 2
ክብርህን ያየሁ ዕለት ልቤን ደስ ይለዋል
ሞገስህን ሳየው ልቤን ደስ ይለዋል
ግርማህንም ሳየው ልቤ ደስ ይለዋል
ፍቅርህን ሳየው ልቤን ደስ ይለዋል
ባለ ግርማ ነህ (፪x) ባለ ግርማ
ባለ ሞገስ ነህ (፪x) ባለ ሞገስ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ