የንጉሥ ቤተሰብ
Yenegus Bieteseb
2010 · ትራክ 9 · 5:08 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አገኘሁ መላ ያለበት ቤት
አገኘሁ ፍርድ የሚሰጥበት
ቁጥር 2 · Verse 2
ለዚህ ነው የተረጋጋሁት (፪x)
ልዑል ነው ልዑል ነው አባቴ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ዝማሬው ይፈልቃል ከቤቴ
እንዴት ይመኛል ልቤማ ሌላ
ተስተናግጄ ከንጉሥ ጋራ
ተቆረሰና የሰላም ማዕድ
ቤቱ ይሞቃል አያስገባም ብርድ
አሃ አሃ ለተጨነቀማ ግራ ለገባዉ
ቁጥር 4 · Verse 4
ትክክለኛው መልስ በእጁ ነው ያለው (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ተራራው ተጋርዶ ፊት ለፊት ሳየው
ጌታ እንዳስለመደኝ እጄን አነሳሁ
በመንፈስ የሆንን አምልኮን ስሰዋ
የት እንደ ሄደ አላውቅም ወዴት እንደገባ
የእኔ ጌታ የእኔ እረኛ
ቁጥር 6 · Verse 6
ለዚህ እኮ ነው የጠራኛ/የቀባኛ (፪x)
ቁጥር 7 · Verse 7
ሊነካኝ አይችልም ጠላቴ (፪x)
እሳቱ ከቦኛል የአባቴ
አትንኩት አትንኩት ይላሉ (፪x)
ይታያል ደሙ በጉበኑ
አትንኳት አትንኳት ይላሉ
አትንኩት አትንኩት ይላሉ
ይታያል ደሙ በጉበኑ
ቁጥር 8 · Verse 8
ጳውሎስና ሲላስ ቢታሰር እጃቸው
አምልኮ አላቆሙም ተፈቷል ውስጣቸው
ሊጠፋ አይችልም ውስጥ ያለው እሳት
እንደውም ይብሳል ሲቆሰቁስት
አዝማች · Chorus
የእኔ ጌታ የእኔ እረኛ
ቁጥር 9 · Verse 9
ለዚህ እኮ ነው የቀባኛ/የጠራኛ (፪x)
ቁጥር 10 · Verse 10
ወዴት ወዴት ወዴት (፪x)
እንዴት እንዴት ይመኛል
እንዴት እንዴት እንዴት
የንጉሥ ቤተሰብ አይመኝም ሌላ
አምሮበት ይኖራል ከእጁ እየበላ
የንጉሥ ቤተሰብ አይመኝም ውጪ
ያበድራል እንጂ አይደለም ተረጂ
አዝማች · Chorus
የእኔ ጌታ የእኔ እረኛ
ቁጥር 11 · Verse 11
ለዚህ እኮ ነው የጠራኛ/የቀባኛ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ