ኢየሱስ ስልህ
Eyesus Seleh
2010 · ትራክ 7 · 5:31 · አማርኛ
የሕይወቴን ጅማሬ የሕይወቴን ፍጻሜ ባረከልኝና
የትላንቱ ኑሮዬን የትላንቱ ኃጢአቴን ይቅር አለኝና
ኑር አለኝ (፫x) ጌታ ኑር አለኝ
ኑር አለኝ (፫x) ጌታ ኑር አለኝ
ልዑል ዓላማ አለው በእኔ ላይ (፪x)
በእኔ ላይ (፬x)
ልዑል ዓላማ አለው በእኔ ላይ (፪x)
በእኔ ላይ (፬x)
በጉዞዬ ግራ እንዳይገባኝ
በሌሊትም በቀን ስትመራኝ
በደመናው በእሳትህ አምደህ
ተከተልከኝ ልቤ . (1) .
ኢየሱስ ስልህ ውድዬ ስልህ
አግዘኝ ስልህ ና እርዳኝ ስልህ
ማዕበሉን ረግጠህ ትመጣልኛለህ
ወጀቡን ረግጠህ ትደርስልኛለህ
ማዕበሉን ረግጠህ ትመጣልኛለህ
ወጀቡን ረግጠህ ትደርስልኛለህ (፪x)
በገና አንስቼ የትንቢት ዜማ ስደረድር
ማምለኬን አውቆ ውኃ ፈለቀ ደረቅ ምድር
ዓይኔን ሲከፍተው ልቤን ሲከፍተው ዙሪያዬን ሳይ
ኢየሱስ ቆሟል ጠላቴ ደፍሮ እንዳይነካኝ
ልዑል ዓላማ አለው በእኔ ላይ (፪x)
በእኔ ላይ (፬x)
ልዑል ዓላማ አለው በእኔ ላይ (፪x)
በእኔ ላይ (፬x)
ምዕራፌ እንዳይዘጋ
የጨለመው ቶሎ እንዲነጋ
በበረሃው ጥላ የሆንከኝ
አንተ እኮ ነህ ከሞት ያዳንከኝ
ኢየሱስ ስልህ ውድዬ ስልህ
አግዘኝ ስልህ ና እርዳኝ ስልህ
ማዕበሉን ረግጠህ ትመጣልኛለህ
ወጀቡን ረግጠህ ትደርስልኛለህ
ማዕበሉን ረግጠህ ትመጣልኛለህ
ወጀቡን ረግጠህ ትደርስልኛለህ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ