ያለመልማል
Yalemelemal
ትራክ 10 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ልምላሚየ ቃልህ ነው
መከናወኔ ሕግህ ነው
የልቤ ደስታ ድምጽህ ነው ጌታየ (2)
ጌታየ (4)
ቁጥር 1 · Verse 1
በድህነቴ ብልጥግናየ
ስርዓትህ ነው ? ተድላየ
ደመናየ ነው የእሳት ኣምዴ
ቅዱሱ ቃልህ መሪ እስከ ርስቴ
አዝማች · Chorus
ልምላሚየ ቃልህ ነው
መከናወኔ ሕግህ ነው
የልቤ ደስታ ድምጽህ ነው ጌታየ (2)
ጌታየ (4)
ቁጥር 2 · Verse 2
ኣቤቱ ቃልህ በልቤ በራ
የሂወት መንገዴ በፊትህ ቀና
ለምለም ስፍራየ የእረፍት ወሀ
ሆኖኛል ሕግህ በምድረበዳ
አዝማች · Chorus
ልምላሚየ ቃልህ ነው
መከናወኔ ሕግህ ነው
የልቤ ደስታ ድምጽህ ነው ጌታየ (2)
ጌታየ (4)
ቁጥር 3 · Verse 3
የኣንተ ቃል መንገድ ያወጣል
ትእዛዝህ በሂወት ያኖራል
ድንቅ ምክርህ ዕድሜን ያረዝማል
ቅዱስ ቃልህ ያለመልማል (2)
አዝማች · Chorus
ልምላሚየ ቃልህ ነው
መከናወኔ ሕግህ ነው
የልቤ ደስታ ድምጽህ ነው ጌታየ (2)
ጌታየ (4)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ