Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የሕይወቴ ዋና

Yehiwotie Wana

ትራክ 8 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ያለ ህልውና ደግሞ ያለ ክብር

መኖር ኣልችልም ያለ መገኘት (2)

ክብርህን ማየት ሁሌ ጥማቴ

ድምጽህን መስማት ነው’ኮ ጉጉቴ

መንፈስህ ነው ለኔ ረሃቤ

መገኘትህ ‘ኮ ነው ለኔ ደስታየ

እባክህ ጌታ ሆይ (እባክህ ጌታ ሆይ)

ሁሉም እኔ ይቅርብኝ

ቅዱስ መንፈስህ (ቅዱስ መንፈስህ)

ከኔ ኣትውሰድብኝ (ከኔ ኣትውሰድብኝ)

ካንተ ተለይቼ መኖር እኔ ኣልችልም

የሂወቴ ዋና ምሶሶ ያንተ ነህ (5)

ስጠራህ ስማኝ (ስጠራህ ስማኝ)

ስፈልግህ ተገኝ (ስፈልግህ ተገኝ)

ሰምተህ እንዳልሰማህ (ሰምተህ እንዳልሰማ)

‘ባክህ ኣትሁንብኝ (‘ባክህ ኣትሁንብኝ)

ያለ መገኘትህ ያለ ህልውናህ

እኔ’ኮ ባዶ ነኝ ያለ መንፈስህ

ክብርህን ማየት ሁሌ ጥማቴ

ድምጽህን መስማት ነው’ኮ ጉጉቴ

መንፈስህ ነው ለኔ ረሃቤ

መገኘትህ ‘ኮ ነው ለኔ ደስታየ

የሂወቴ ዋና ምሶሶ ያንተ ነህ (5)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ