አቤት እንዴት ውብ ነው
Abiet Endiet Wub New
2010 · ትራክ 4 · 5:41 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አቤት እንዴት ውብ ነው እንዴትስ ድንቅ ነው
አቤት እንዴት ውብ ነው እንዴትስ ድንቅ ነው
ጊዜውን ጠብቀህ ይሁን ብለህ ያልከው
ጊዜውን ጠብቀህ ይሁን ብለህ ያልከው (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
አቤት እንዴት ፣ እንዴት : ውብ ነው
እንዴት ውብ ነው ግሩም ነዉ
መጨረሻው እጅግ ያምራል እግዚአብሔር የሰራዉ (፪x)
አላየሁም በዘመኔ
አስደናቂ ነው ሥራ ለእኔ (፪x)
አዝማች · Chorus
አቤት እንዴት ውብ ነው እንዴትስ ድንቅ ነው
አቤት እንዴት ውብ ነው እንዴትስ ድንቅ ነው
ጊዜውን ጠብቀህ ይሁን ብለህ ያልከው
ጊዜውን ጠብቀህ ይሁን ብለህ ያልከው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አስደናቂ ነገር አንተ አድርገሃል
አውቃለሁ ጌታዬ ሥራው ያስታውቃል (፪x)
በሙሉ: ይሁን ያልከው ፀንቶ ቀረ ያዘዝከው
ይኼ ሁሉ በአንተ ነው ፣ ይኼ ሁሉ በአንተ ነው (፪x)
አላየሁም በዘመኔ
አስደናቂ ነው ሥራ ለእኔ (፪x)
አዝማች · Chorus
አቤት እንዴት ውብ ነው እንዴትስ ድንቅ ነው
አቤት እንዴት ውብ ነው እንዴትስ ድንቅ ነው
ጊዜውን ጠብቀህ ይሁን ብለህ ያልከው
ጊዜውን ጠብቀህ ይሁን ብለህ ያልከው (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አቤት እንዴት ፣ እንዴት ውብ ነው
እንዴት ውብ ነው ግሩም ነዉ
መጨረሻው እጅግ ያምራል እግዚአብሔር የሰራዉ (፪x)
በሙሉ: ይሁን ያልከው ፀንቶ ቀረ ያዘዝከው
ይኼ ሁሉ በአንተ ነው ፣ ይኼ ሁሉ በአንተ ነው (፭x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ