በበረከት የሚኖር
Bebereket Yeminor
2010 · ትራክ 9 · 4:26 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሠማዩ የአንተ ነው ፣ የአንተ ነው
ምድሩ የአንተ ነው ፣ የአንተ ነው (፪x)
ባለጠግነትህ ዓለምን ሸፈነው (፬x)
በበረከት የሚኖር ግርማው የሚያስፈራ
ድህነትን የማያውቅ ችግር የማይፈራ
በዘመናት መሃከል እንደ አንተ ያለ ማነው
አዝማች · Chorus
ባለጠጋ መሆንክህን እኔ እናገራለሁ (፪x)
ባለጠግነትህ ዓለምን ሸፈነው (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የእኔ አምላክ ክብር ያለዉ ክብር ያለው
አምላኬ ሞገስ ያለው ሞገስ ያለዉ (፪x)
ክብር ያለው ሞገስ ያለዉ
ሁሉም ያለው (፬x)
አዝማች · Chorus
ባለጠግነትህ ዓለምን ሸፈነው (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ባህሪህ መልካም ነው
ግሩም ነው ድንቅ ነው
አንተን ተመልክቶ እማይወድ ማነው
አዝማች · Chorus
አቤት የእኔ ጌታ ፣ አቤት የእኔ ጌታ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ