Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ሃሌሉያ

Hallelujah

2010 · ትራክ 11 · 5:28 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ሃሌሉያ (፰x)

ሕይወቴን በእጁ የያዘ መንገዴን የሚቀይሰው

አምላኬ እርሱ ብቻ ነዉ እግዚአብሔር እርሱ ብቻ ነዉ

ሕይወቴን ሰጥቸዋለሁ መልሼ ከእጁ አልወስደዉም

ከእንግዲህ ሕይወት የለኝም ሕይወቴ እርሱ ብቻ ነዉ

ሃሌሉያ (፰x)

አረጋግጣለሁ በከንፈሬ ቃል

በልቤ በሃሳቤ መቼ ይበቃል

በጉባኤው መሃል ፍቅሬን አዉጃለሁ

እኔ የእግዚአብሔር ነኝ እወቁት እላለሁ (፪x)

ሃሌሉያ (፰x)

የገባዉ ሰዉ በአንተ መታየቱ

መወደዱ ደህንነት ማግኘቱ

ሳይለመን ሁሌ ያመልክሃል

በአንደበቱ ክብርን ይሰጥሃል (፪x)

አረጋግጣለሁ በከንፈሬ ቃል

በልቤ በሃሳቤ መቼ ይርቃል

በጉባኤው መሃል ፍቅሬን አዉጃለሁ

እኔ የእግዚአብሔር ነኝ እወቁት እላለሁ (፪x)

ሃሌሉያ (፰x)

የገባዉ ሰዉ በአንተ መታየቱ

መወደዱ ደህንነት ማግኘቱ

ሳይለመን ሁሌ ያመልክሃል

በአንደበቱ ክብርን ይሰጥሃል (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ