Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ደህና ነኝ

Dehna Negn

2010 · ትራክ 12 · 5:28 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ቀናቶቼ በከንቱ ዓመታቶቼ በችኮላ

እንዲሁ እንዳያልፉ ከዚህ በኋላ

ዘመኔን በሙሉ በፊቴ ያለውን

ያለ ፍሬ እንዳልሆን አስታጥቀኝ ኃይልን

ደህና ደህና ነኝ እግዚአብሔር ይመስገን (፭x)

ደህና ደህና ነኝ እግዚአብሔር ይመስገን (፭x)

የሕይወቴን መጸሃፍ የጻፈው እግዚአብሔር

ደራሲው እርሱ ነው ተራኪዋ እኔ ነኝ (፪x)

የመጨረሻውን ምዕራፉን ሳነበው

ደህና ነሽ በሎኛል ደህና ነኝ እላለው (፪x)

ደህና ደህና ነኝ እግዚአብሔር ይመስገን (፭x)

ደህና ደህና ነኝ እግዚአብሔር ይመስገን (፭x)

ሳለ መድሃኒያለም በዙፋኑ ላይ

በቀኝም በግራም ሠላም አይደል ወይ (፪x)

እግዚአብሔር ይመስገን እፎይ ብያለሁ

በአገሪቱ ላይ ተዘልያለሁ (፪x)

ደህና ደህና ነኝ እግዚአብሔር ይመስገን (፭x)

ደህና ደህና ነኝ እግዚአብሔር ይመስገን (፭x)

እግዚአብሔር አምላኬ ደህንነት ሆነልኝ

እግዚአብሔር አምላኬ እፎይታ ሆነልኝ

እግዚአብሔር አምላኬ ጸጥታ ሆነልኝ

እግዚአብሔር አምላኬ ሠላሜ ሆነልኝ

ደህና ደህና ነኝ እግዚአብሔር ይመስገን (፭x)

ደህና ደህና ነኝ እግዚአብሔር ይመስገን (፭x)

ምሥጋና የሚገባው አምልኮ የሚገባው

ዝማሬ የሚገባው እግዚአብሔር አምላኬ ነው (፪x)

አምልኮ የሚገባው እግዚአብሔር አምላኬ ነው

መምስገን የሚገባው እግዚአብሔር አምላኬ ነው

መወደድ የሚገባው እግዚአብሔር አምላኬ ነው

መከብር የሚገባው እግዚአብሔር አምላኬ ነው

እግዚአብሔር አምላኬ ነው (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ