Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አምልኮህ ያፈረ የለም

Amlekoh Yafere Yelem

2010 · ትራክ 2 · 5:26 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አሁንም : እህሌን ውኃዬን ባርከሃል አሃሃ

በሽታን ከቤቴ ከደጄ አርቀሃል (፪x)

የዘመኔን ቁጥር ሞልተሃል ኦሆሆ

የዘመኔን ቁጥር ሞልተሃል አሃሃ (፪x)

አመልክሃለው ወድጄ አመልክሃለው ፈቅጄ (፬x)

አምልኮህ ያፈረ የለም አንተን አሞጋግሶ

እዚያው ቀርቷል እንጂ ክብርህ ጋር ደርሶ (፪x)

አምልኮህ ያፈረ የለም አንተን አሞጋግሶ

እዚያው ቀርቷል እንጂ ክብርህ ጋር ደርሶ (፬x)

አምልኮህ አምልኮህ አንተን ወዶህ ወዶህ

አንተን ወዶህ ወዶህ

ማን የቀረ አለ ከበረከት ማዶ

ከበረከት ማዶ (፪x)

አሁንም እህሌን ውኃዬን ባርከሃል አሃሃ

በሽታን ከቤቴ ከደጄ አርቀሃል (፪x)

የዘመኔን ቁጥር ሞልተሃል ኦሆሆ

የዘመኔን ቁጥር ሞልተሃል አሃሃ (፪x)

አምልኮህ ያፈረ የለም አንተን አሞጋግሶ

እዚያው ቀርቷል እንጂ ክብርህ ጋር ደርሶ (፪x)

ጸልዮ ያፈረ የለም አንተን ተለማምጦ

ተቀብሏል እንጂ ከሁሉ አብልጦ (፬x)

አመልክሃለው ወድጄ አመልክሃለው ፈቅጄ (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ