ቅዱስ እግዚአብሔር
Qedus Egziabhier
2010 · ትራክ 5 · 7:33 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
ንጹህ ፍፁም ነውር የሌለህ (፪x)
አንተ ነውር የለህም
አንተ እድፈት የለህም
አንተ ጉድለት የለህም
አንተ እንከን የለህም (፪x)
አንተ ራስህ እውነት ነህ
ምንም ውሸት የለብህ
ኦ የለብህ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
ንጹህ ፍፁም ነውር የሌለህ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አንተ ነውር የለህም
አንተ እድፈት የለህም
አንተ ጉድለት የለህም
አንተ እንከን የለህም (፪x)
ታድያ እኔ ተስፋዬ ማነው
እግዚአብሔር አይደለም ዎይ (፪x)
አሁንስ ተስፋዬ ማነው
እግዚአብሔር አይደለም ዎይ (፪x)
ጠቢብ በጥበቡ አይመካ
ኃያልም በኃይሉ አይመካ
ፍርድንና ጽድቅን በምድር ላይ የሚያደርግ
እርሱ መሆኑን በማወቁ ብቻ
በዚያ ይመካ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አውቄያለሁና ጠንቅቄ
ያላንተ ተስፋ እንደሌለኝ
ያላንተ ተስፋ እንደሌለኝ (፪x)
አንተን የታመነ ሰው ሌላ ሌላ ሳይደምር/ሳይጨምር
የተረጋገጠ ነው ፍጻሜው እንደሚያምር (፪x)
ታድያ እኔ ተስፋዬ ማነው
እግዚአብሔር አይደለም ዎይ (፪x)
አሁንስ ተስፋዬ ማነው
እግዚአብሔር አይደለም ዎይ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
አዋቂው በዕውቀቱ አይመካ
ጻድቁም በጽድቁ አይመካ
ፀላይም በፀሎቱ አይመካ
ጿሚዉም በመጾሙ አይመካ
ፍርድንና ጽድቅን በምድር ላይ የሚያደርግ
እርሱ መሆኑን በማወቁ ብቻ
በእርሱ ይመካ (፪x)
አዝማች · Chorus
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
ንጹህ ፍፁም ነውር የሌለህ (፪x)
አንተ ነውር የለህም
አንተ እድፈት የለህም
አንተ ጉድለት የለህም
አንተ እንከን የለህም (፪x)
አንተ ራስህ እውነት ነህ
ምንም ውሸት የለብህ
ኦ የለብህ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ