ለእግዚአብሔር ቀላል ነው
LeEgziabhier Qelal New
2010 · ትራክ 1 · 4:41 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ይህም በእግዚአብሔር ዓይን ቀላል ነው ቀላል
ይህም በአምላኬ ዓይን ቀላል ነው (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ቀላል ነው ፣ ቀላል ነው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ከባድ የሚባል ነገር አታውቅም
ትልቅ የሚባል ነገር አታውቅም
አስፈሪ የሚባል ነገር አታውቅም
አልችልም የሚል ቃልን አታውቅም
ስለዚህ ዝም ብዬ አመልክሃለሁ
ስለዚህ ዝም ብዬ እደሰታለሁ
ስለዚህ ዝም ብዬ እጸልያለሁ
ስለዚህ ዝም ብዬ አከብርሃልሁ
ቁጥር 3 · Verse 3
አመልክሃለው ፣ አመልክሃለው (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
አንተ እኮ ነህ መልሱን የነገርከኝ
ምንም እንዳይመስለኝ ያደረከኝ
እስከሚገርመኝ ድርስ እደሰታለሁ
ከባዱ ፈተና ለካ ቀላል ነው
ቁጥር 5 · Verse 5
ይህም በአምላኬ ዓይን ምንም ነው ምንም
ይህም በአምላኬ ዓይን ምንም ነው
ይህም በአምላኬ ዓይን ቀላል ነው ቀላል
ይህም በአምላኬ ዓይን ቀላል ነው
ቀላል ነው ፣ ቀላል ነው
ምንም ነው ፣ ምንም ነው
ቁጥር 6 · Verse 6
ከባድ የሚባል ነገር አታውቅም
ትልቅ የሚባል ነገር አታውቅም
አስፈሪ የሚባል ነገር አታውቅም
ምንም መጣ ብለህ አትደነግጥም
ስለዚህ ዝም ብዬ አመልክሃለሁ
ስለዚህ ዝም ብዬ እደሰታለሁ
ስለዚህ ዝም ብዬ እጸልያለሁ
ስለዚህ ዝም ብዬ እጠብቅሃለሁ
ቁጥር 7 · Verse 7
አመልክሃለው አከብርሃለሁ
እደሰታለሁ እጸልያለሁ
ቁጥር 8 · Verse 8
የለም የሚባል ነገር አታውቅም
አልቋል የሚባል ነገር አታውቅም
አልችልም የሚል ቃልን አታውቅም
አይሆንም የሚል ቃልን አታውቅም
ስለዚህ ዝም ብዬ አመልክሃለሁ
ስለዚህ ዝም ብዬ አከብርሃልሁ
ስለዚህ ዝም ብዬ እደሰታለሁ
ስለዚህ ዝም ብዬ እጸልያለሁ
ቁጥር 9 · Verse 9
እጸልያለሁ አከብርሃልሁ
እጠብቃለሁ እደሰታለሁ
አዝማች · Chorus
ይህም በእግዚአብሔር ዓይን ቀላል ነው ቀላል
ይህም በአምላኬ ዓይን ቀላል ነው
ቁጥር 10 · Verse 10
ይህም በአምላኬ ዓይን ምንም ነው ምንም
ይህም በእግዚአብሔር ዓይን ምንም ነው
ኧረ በእግዚአብሔር ምንም ነው ምንም
ኧረ በአምላኬ ምንም ነው
ምንም ነው ፣ ምንም ነው (፪x)
ቀላል ነው ፣ ቀላል ነው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ