Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ለካ ምሕረትህ ነው

Leka Mehereteh New

2010 · ትራክ 13 · 4:55 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ለካ ምህረትህ ነው የሚደጋግፈኝ

ለካ ይቅርታህ ነው እኔን የሚያቆመኝ

ለካ ፍቅርህ ነው የሚያጠነክረኝ

ለካ ክብርህ ነው ውበት የሚሆነኝ

ከወርቅ ከዕንቁ ይልቅ ጌታ ይሻለኛል

ማለዳ ማለዳ ምህረት ያጠግበኛል (፪x)

ማለዳ ማለዳ ሠላም ያሰጠኛል

ማለዳ ማለዳ ፍቅር ያጠግበኛል

ማለዳ ማለዳ ጤና ያሰጠኛል

በምን ቃል ልናገር በምን ቋንቋ ላውራ

ከአይምሮ በላይ ነው ጌታ የአንተ ሥራ (፪x)

ብዙ ብዙ ብዙ ብዙም ሚለው ቃል ከገለጸው

የፍቅርን ብዛት ብዙ ነው ብዬ እናገራለሁ

ብዙ ብዙ ብዙ ብዙም ሚለው ቃል ከገለጠው

የስጦታን ብዛት ብዙ ነው ብዬ እናገራለሁ

ለካ ምህረትህ ነው የሚደጋግፈኝ

ለካ ይቅርታህ ነው እኔን የሚያቆመኝ

ለካ ፍቅርህ ነው የሚያጠነክረኝ

ለካ ክብርህ ነው ውበት የሚሆነኝ

ከወርቅ ከዕንቁ ይልቅ ጌታ ይሻለኛል

ማለዳ ማለዳ ምህረት ያጠግበኛል (፪x)

ማለዳ ማለዳ ደስታ ያሰጠኛል

በምን ቃል ልናገር በምን ቋንቋ ላውራ

ከአይምሮ በላይ ነው ጌታ የአንተ ሥራ (፪x)

ብዙ ብዙ ብዙ ብዙም ሚለው ቃል ከገለጸው

የፍቅርን ብዛት ብዙ ነው ብዬ እናገራለሁ

ብዙ ብዙ ብዙ ብዙም ሚለው ቃል ከገለጠው

የይቅርታን ብዛት ብዙ ነው ብዬ እናገራለሁ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ