ምርኩዜ
Merkuzie
2010 · ትራክ 10 · 6:07 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ምርኩዜ ሸንበቆ አይደለም ፣ አይደለም (፪x)
ምርኩዜ ሸንበቆ አይደለም (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ይብላኝ አምላክ ለሌለው
መታመኛ የሚሆነው
እኔስ አምላክ አለኝ
እሚያስተማምነኝ (፪x)
በምንም ተዓምር አላቋርጥም
በአንተ መመካቴ እኔ አላቆምም (፪x)
ምርኩዝዬ አንተ ታስፈልገኛለህ
እስከ መጨረሻው እኔን ታቆማለህ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ይብላኝ ይብላኝለት ፣ ይብላኝለት
አምላክ ለሌለው (፪x)
እኔስ አምላክ አለኝ እሚያስተማምነኝ
እኔስ አባት አለኝ አይዞሽ ልጄ ይለኝ
እኔስ ጌታ አለኝ እሚያስተማምነኝ
በምንም ተዓምር አላቆምም
በአንተ መመካቴ እኔ አላቋርጥም (፪x)
ምርኩዝዬ አንተ ታስፈልገኛለህ
እስከ መጨረሻው ታዛልቀኛለህ (፪x)
አዝማች · Chorus
ምርኩዜ ሸንበቆ አይደለም (አይደለም) (፪x)
ምርኩዜ ሸንበቆ አይደለም (አይደለም) (፪x)
ምርኩዜ ሸንበቆ አይደለም (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ይብላኝ አምላክ ለሌለው መታመኛ የሚሆነው
እኔስ አምላክ አለኝ እሚያስተማምነኝ (፪x)
ይብላኝ ይብላኝለት ፣ ይብላኝለት
ኢየሱስ/አዳኝ ለሌለው (፪x)
እኔስ ኢየሱስ አለኝ ሕይወቱን የሰጠኝ
እኔስ አዳኝ አለኝ ጉልበቱን የሰጠኝ
እኔስ ኢየሱስ አለኝ ሕይወቱን የሰጠኝ
አዝማች · Chorus
ምርኩዝህ ሸንበቆ አይደለም (አይደለም) (፪x)
ምርኩዝሽ ሸንበቆ አይደለም (አይደለም) (፪x)
አይደለም (አይደለም) (፬x)
ምርኩዝህ ሸንበቆ አይደለም
ምርኩዝሽ ሸንበቆ አይደለም
አይደለም (፰x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ